በአቤኔዘር አበበ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን አሳካ

በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሦስተኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን 1–0 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል አስመዝግቧል።ጨዋታው እንደተጀመረ ግብ ያስቆጠረው ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ በሦስተኛው ካሌብ ሴትፍሜልቪን መረብ ላይ በማሳረፍ ቡድኑን መሪ አድርጓል።ከግቡ በኋላ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል በተደጋጋሚ ቢደርሱም ተጨማሪ ግብ ሳያስቆጥሩ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።በሁለተኛው አጋማሽ ሸገር ከተማ ውጤቱን ለመቀየር ጥረት ቢያደርግም የኢትዮ ኤሌክትሪክን መከላከል ማለፍ አልቻለም። በዚህም ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአንድ ግብ ልዩነት ድሉን አረጋግጧል።
የሙሉ ሰዓት ውጤት
ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1–0 ሸገር ከተማ
⚽️ 3′ ካሌብ ሴትፍሜልቪን
አስተያየት ይስጡ