መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ተራዘመ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ተራዘመ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ለአንድ ሳምንት መራዘሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለጸ።የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ፕሮግራም ደግሞ ወደ ጥቅምት ሰባት መራዘሙን ፌደሬሽኑ አስታውቋል።

የፌዴሬሽኑ የውደድርና ተሳትፎ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ ለኢዜአ እንደገለጹት ሊጉ የሚጀመርበት ቀን ሊራዘም የቻለው የአዲስ አበባ ስታዲየም ጭቃ በመሆኑ ውድድር ማስተናገድ ስለማይችልና ሌሎች የሲቲ ካፕ ውድድሮች በመኖራቸው ነው።
የሲቲ ካፕ ውድድሮች በደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚደረጉ ናቸው።
በእነዚህ ምክንያቶች ሊጉ ከጥቅምት አራት ወደ ጥቅምት አስራ አንድ መራዘሙን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል።
መስከረም 27 ለማካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ጥቅምት ሰባት እንዲካሄድ ተወስኗል።
በ1990 ዓም በአዲስ መልክ የተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአስራ ስድስት ክለቦች መካከል የሚደረግ ነው።
ምንጭ -ኢዜአ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የሚዲያ ኦፊሰሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ

ለፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ ስልጠና ተሰጠ የኢትዮጵያ እግር...

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየዝውውር ዜናዎች

እዮብ አለማየሁ ለወልዋሎ እንዲጫወት ተወሰነ

እዮብ አለማየሁ ጉዳይ  ውሳኔ አገኘ። ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱ ተጫዋቾች ለመቻል እንዲጫወቱ ሲወሰን ቅጣትም ተጣለባቸው

አለምብርሀን ይግዛው እና አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ ጉዳይ ውሳኔ አገኘ። በያዝነው የክረምቱ የዝውውር...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፌደሬሽኑን ለ3ኛ ጊዜ ለመምራት ብቸኛ እጩ ሆነው ቀርበዋል።

እጩ ሆኜ መቅረቤን እንጂ ሌሎች ተፎካካሪዎች ለምን በፕሬዝደንትንት ለመወዳደር እንዳልቀረቡ የማውቀው ነገር...