መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ 9ኛው የመላ ኣፍሪካ ዩኒቨርስቲ ጨዋታዎች ተጠናቀቀ
መቐለ ከተማመቐለ ዮንቨርሲቲየመላው አፍሪካ ጨዋታየትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

9ኛው የመላ ኣፍሪካ ዩኒቨርስቲ ጨዋታዎች ተጠናቀቀ

አጋራ
አጋራ

ባሳለፍነው እሁድ በመቐለ ዩኒቨርስቲ ኣስተናጋጅነት በደማቅ ስነ-ስርዓት የተከፈተው 9ኛው የመላ ኣፍሪካ ዩኒቨርስቲ ጨዋታዎች ትላንት በመቐለ ዩኒቨርስቲ ዓዲ ሓቂ ካምፓስ ላይ በተደረገ ያማረ የመዝግያ ስነ-ስርዓት ተጠናቋል።በመዝግያው ስነ-ስርዓት ከውስጥ እና ከውጭ ሃገር የተጋበዙ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

58 የኣፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች በተሳተፋበት በዚህ ውድድር ከ ስፓርታዊ ውድድር ውጪ የባህልና የቴክኖሎጂ ልውውጦች የተካሄደበት ነበር።መቐለ ዩኒቨርሲቲም ኣፍሪካውያን በኣንድ መንደር የተሰባሰቡበትን ዝግጅት በሙሉ ብቃት ኣስተናግዳ ጨርሳለች።

NDDEJJE ዩኒቨርስቲ በኣጠቃላይ ውድድሩ ላይ በኣገኛቸው 10 ወርቅ፣4 ብር እና 5 ነሃስ በኣጠቃላይ 19 ሜዳልያዎች የውድድሩ ኣሸናፊ ሆኗል።ኢትዮጵያን ከወከሉ 11 ዩኒቨርስቲዎችም ኣዲስኣበባ ዩኒቨርስቲ ባገኛቸው 8 ወርቅ፣6 ብር እና 11 ነሃስ ሦስተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።

ብዙ ተመልካች የተከታተለው የወንዶች እግር ኳስ በዛንዚባር ዩኒቨርስቲ ኣሸናፊነት ተጠናቋል።በፍፃሜው ጨዋታ ኮተቤ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅን የገጠሙት ዛንዚባሮች ሦስት ለኣንድ በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳት ችለዋል።

የሃገራት የሜዳልያ ደረጃን ኡጋንዳ ኢትዮጵያ ና ጋና በቅደም ተከተል ከኣንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ኣጠናቀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የሊጉን አስተዳደር ማብራሪያ ጠይቋል

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የክለቦች ደንብን ያልተከተለ የገንዘብ ክፍያን ተከትሎ በሰጠው ጋዜጣዊ...

መቐለ ከተማዜናዎች

መቐለ ላይ ሀትሪክ ተሰራ ኦኪኪ አፎላቢ ሀዋሳ ላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

መቐለ ላይ ሀትሪክ ተሰራ ኦኪኪ አፎላቢ ሀዋሳ ላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ...

ትግራይ ዋንጫዜናዎችየትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ትግራይ ዋንጫ |ሲዳማ ቡና ከሰሎዳ ዓድዋ ጋር ነጥብ ተጋርተዋል

አራተኛ ቀኑን በያዘው ትግራይ ዋንጫ ሥስት ክለቦችን በያዘው ምድብ ሁለት ሲዳማ ቡና...