በሀገሪቱ ተከስቶ በነበረዉ ጦርነት ምክንያት በፕሪሚየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ በመሳሰሉ ዉድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበሩት ክለቦች ከውድድር ዉጭ መሆናቸዉ የሚታወስ ሲሆን ፤ አሁን ላይ ግን በሀገሪቱ በተፈጠረው ሰላም መሰረት የትግራይ ክልል ክለቦች ወደ ዉድድር እንደሚለሱ የክልሉ እግርኳስ ፌደሬሽን ለሚመለከታቸዉ አካላት ጥያቄ አቅርቧል።
በዚህም መቀለ 70 እንደርታ ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ስሁል ሽሬን የመሳሰሉ በሊጉ ተሳታፊ የነበሩት ክለቦች እንዲሁም በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ፣ብሔራዊ ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የነበሩ ወደ ዘጠኝ የሚደርሱ ክለቦች በጦርነቱ ምክነያት በደረሰባቸው ውድመት ምክንያት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፣ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን አስፈላጊዉን ድጋፍ አድርገዉላቸዉ በ2016 ወደ ውድድር እንዲመለሱ የክልሉ እግርኳስ ፌደሬሽን በደብዳቤ ጠይቋል።