14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቀጥሎ ተካሂዷል።
አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ወደ ይርጋለም ያቀናው ደደቢት ደግሞ በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ በተቆጠሩበት ሁለት ጎሎች በሲዳማ ቡና 2 ለ 0 ተሸንፏል።
ሃዋሳ ላይ ጅማ አባቡናን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
በጨዋታው ጅማ አባ ቡና 1 ለ 0 መምራት ቢችልም፥ ሃዋሳ ከተማ በተከታታይ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።
አርባ ምንጭ ከተማ ከወላይታ ዲቻ ያደረጉት ጨዋታም ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ወልድያ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያስተናገደበት ጨዋታ ደግሞ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት አጠናቋል፡፡
አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ከተማ ያደረጉት ጨዋታም በተመሳሳይ 1 ለ 1 ተጠናቋል።
ድሬዳዋ ላይ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ፋሲል ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ደረጃ ሰንጠረዥ
| # | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
|---|---|---|---|---|
| 1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ |
14 | 13 | 26 |
| 2 | አዳማ ከተማ |
14 | 5 | 26 |
| 3 | ደደቢት |
13 | 8 | 24 |
| 4 | ሲዳማ ቡና |
14 | 2 | 24 |
| 5 | ኢትዮጵያ ቡና |
14 | 3 | 23 |
| 6 | አርባምንጭ ከተማ |
14 | 3 | 21 |
| 7 | ፋሲል ከተማ |
13 | 4 | 20 |
| 8 | መከላከያ |
14 | -1 | 20 |
| 9 | ወልድያ |
14 | 0 | 18 |
| 10 | ወላይታ ድቻ |
13 | 0 | 17 |
| 11 | ድሬዳዋ ከተማ |
14 | -5 | 15 |
| 12 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
13 | -4 | 13 |
| 13 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ |
14 | -4 | 12 |
| 14 | ሀዋሳ ከተማ |
13 | -6 | 11 |
| 15 | ጅማ አባ ቡና |
14 | -8 | 10 |
| 16 | አዲስ አበባ ከተማ |
14 | -8 | 9 |




















አስተያየት ይስጡ