የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ዘንድሮ የተቀላቀለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ቡድን የክለቡን ስራ አስኪያጅ ጨምሮ ቴክኒካል ዳይሬክተሩን የቡድን መሪውንና የሂሳብ ሰራተኛውን በአስቸካይና ጥድፊያ በሆነ ድንገተኛ ውሳኔ ስራ እንዲያቆሙ አዟል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በአምስት ዓመታት የምስረታ ጊዜው ሊቀላቀል የቻለው ይኸው ክለብ ቡድኑን ለአራት ዓመታት የመሩትንና ከቡድኑ አሰልጣኝ እና አመራሮች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው ሲነገርላቸው የነበሩትን ስራ
አስኪያጁን አቶ እንዳለየሱስ አባተን እንደዚሁም ቴክኒካል ዳይሬክተሩን
አቶ አበራ ሀብቴን እና ሌሎቹ ሁለቱ የክለቡ ሰራተኞችን ከቦታቸው እንዲለቁ ከውሳኔ ላይ እንደደረሰ የሚነገረው በአዲስ የመዋቅር ለውጥ ሊጓዝ እንደሆነ እና ሌሎች ሰዎችንም በእነሱ ምትክ ለማምጣት እንደሆነ ቢነገርም ቡድኑ ሊጉን ከተቀላቀለበት አጭር ጊዜ አንፃርና ቡድኑ ዝግጅት ገና ሳይጀምርም ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግም ሊጀመር
እየተቃረበ ባለበት ሰዓት ያለምንም የሽግግር ጊዜያት እና ውይይት የተወሰነው ውሳኔ አነጋጋሪ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በጉዳዮ ዙሪያ በቀጣይነት የሚመለከታቸውን አካላት አናግረን ሰፊ ዘገባዎችን ይዘንላችሁ የምንመጣ ይሆናል፡፡