JOHANNESBURG, SOUTH AFRICA - MARCH 19: Fikru Lemessa during the Absa Premiership match between Highlands Park and Maritzburg United at Makhulong Stadium on March 19, 2017 in Johannesburg, South Africa. (Photo by Lefty Shivambu/Gallo Images)
መነሻ ገጽ Uncategorized ፍቅሩ ተፈራ የደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሰንዳውንስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከባድ ፈተና ይጠብቃቸዋል ሲል አስጠነቀቀ፤”በጣም ዝነኛ፣ታላቅና ውጤታማ መሆኑ በራሱ ቅ.ጊዮርጊስ ምን አይነት ክለብ እንደሆነ ይናገራል።”
Uncategorizedሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ፍቅሩ ተፈራ የደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሰንዳውንስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከባድ ፈተና ይጠብቃቸዋል ሲል አስጠነቀቀ፤”በጣም ዝነኛ፣ታላቅና ውጤታማ መሆኑ በራሱ ቅ.ጊዮርጊስ ምን አይነት ክለብ እንደሆነ ይናገራል።”

አጋራ
አጋራ

የቀድሞ የቅ.ጊዮርጊስ የፊት አጥቂ የነበረው ፍቅሩ ተፈራ የደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሰንዳውንስ በቅዳሜው ጨዋታ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል ሲል አስጠነቀቀ።

የቅ.ጊዮርጊስ ማሊያን ለሁለት ዓመታት ለብሶ በሁለቱም ዓመታት የሀገሪቱን ትልቁን ዋንጫ ለመሳም የታደለው ኢትዮጵያዊው ፍቅሩ ተፈራ በደቡብ አፍሪካ በርካታ ተከታታዮች ላሉት “kickoff.com”ለተባለ ድረ-ገፅ በሰጠው መግለጫ ማማሎዲ ሰንዳውንስ ከቅ.ጊዮርጊስ ከባድ ፈተና እንደሚጠብቀውና ጨዋታው በፍፁም ቀላል እንደማይሆን ማስጠንቀቂያ የሚመስል አስተያየቱን ሰጥቷል።
“ማማሎዲ ሰንዳውንስ በቅዳሜ ምሽቱ ጨዋታ በጣም ይፈተናል፤ቀላል ጨዋታም አይጠብቀውም” በማለት አስተያየት መሰጠቱን የጀመረው ፍቅሩ ተፈራ “ቅ.ጊዮርጊስ በጣም ትልቅ ክለብ ነው የቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ውስጥም የገባው በዕድል አይደለም በማጣሪያው የኮንጎ ብራዛቪሉን AC leopards ን በአስገራሚ ሁኔታ 3ለ0 በሆነ አጠቃላይ ውጤት አሸንፎ ከውድድር ያስወጣ ኃያል ነው”በማለት አሰተያየቱን የቀጠለው ፍቅሩ ተፈራ “የቅ.ጊዮርጊስን የአሁኑን ቡድን ተመልክቼዋለሁ በተከላካይም ሆነ በአጥቂ መስመር ላይ በጣም አቅም ያላቸውን ምርጥ ተጫዋቾችን የያዘ ቡድን ነው የገነቡት፤ከዚህ በመነሳት ለማማሎዲ ሰንዳውንስ ብርቱ ፈተና የማይሆኑበትን ምክንያት አላገኘሁም።”ያለው ፍቅሩ “ዕመኑኝ ቅ.ጊዮርጊሶች ከታች ተነስተው ታላቅ መሆን የሚችሉበት አቅሙ አላቸው ልክ ሰንዳውንስ ባለፈው ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ ባለ ድል እንደሆነው ሁሉ”ብላል ለድረ-ገፁ።
“ቅ.ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ ስታንዳርድ ትልቅ አቅም ያለው፣የሀገር ውስጥ ምርጥ ተጫዋቾችን የያዘ ክለብ ነው ከውጪም የፈለጉትን ተጫዋቾች የማምጣት አቅሙ አላቸው የፋይናንስ ጡንቻቸውም በጣም የፈረጠመ ነው ምክንያቱም የክለቡ የበላይ ጠባቂ ሼክ መሀመድ አሊ አል-አሙዲ ከሰንዳውንስ ባለቤት የበለጠ ትልቅ አቅም ያላቸው ናቸውና”ያለው ፍቅሩ ተፈራ
“ቅ.ጊዮርጊሶች ምንም እንኳን ጨዋታቸው ከሜዳቸው ውጪ ቢሆንም ልክ በሜዳቸው የሚጫወቱ ያህል ነው የሚቆጠረው፤ምክንያቱም በስታዲየም የሚገኘው የተመልካች ቁጥር ከፍተኛ ሰለሚሆን”ያለው ፍቅሩ “በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ነው እኔም በሉካስ ሞራፒ ስታዲየም ተገኝቼ የሀገሬንና የቀድሞ ክለቤን እደግፋለሁ”በማለት ፍቅሩ ከkickoff.com ድረ-ገፅ ጋር የነበረውን ቆይታ አጠናቃል።


ከዚሁ ከቅ.ጊዮርጊስ ዜና ጋር በተያያዘ ቡድኑ ጆሃንስበርግ ሲደርስ በክለቡ ደጋፌዎችና እዛ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከአቀባበል ስነስርዓቱ በኋላ ወዲያውኑ ወደ ፕሪቶሪያ በማምራት ወደ ተዘጋጀላቸው ሆቴል ማለትም በሸራተን ሆቴል ማረፋቸው ታውቃል።


መቀመጫውን ፕሪቶሪያ ሸራተን ሆቴል ያደረገው ቅ.ጊዮርጊስ ትናንት ማምሻውን ልምምዳቸውን የሰሩ ዛሬ ከምሳ በኃላ ደግሞ ነገ ጨዋታውን በሚያደርጉበት በሉካስ ሞራፒ ስታድየም መስራታቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችላል።


ነገ በኢትዮጵያ ሠዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1:00 ላይ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀውን የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ እንዲመሩ ሶስት ግብፃውያን ዳኛች ተመድበዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...