መነሻ ገጽ Uncategorized ፌዴሬሽኑ የዕድሜ ተገቢነት ድንገተኛ ማጣራት ማድረግ ጀመረ
Uncategorized

ፌዴሬሽኑ የዕድሜ ተገቢነት ድንገተኛ ማጣራት ማድረግ ጀመረ

አጋራ
አጋራ

ፌዴሬሽኑ የዕድሜ ተገቢነት ድንገተኛ ማጣራት ማድረግ ጀመረ የዕድሜን ተገቢነት ችግር ለመፍታት ድንገተኛ ማጣራት ማድረግ መጀመሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለጸ።

ፌዴሬሽኑ በኢትዮጵያ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ስፖርተኞችን የዕድሜ ተገቢነት ድንገተኛ የማጣራት ስራ ትናንት መጀመሩን ገልጿል።

የኤም.አር.አይ እና አካላዊ የዕድሜ ተገቢነት ምርመራው ከስፖርት ህክምና ቋሚ ኮሚቴና ከውድድር ዳይሬክቶሬት በተውጣጡ ሙያተኞች በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጫዋቾች ላይ ነው ::

በመካሄድ ላይ ያለው በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ተጨዋቾች በትክክለኛው የምርመራ ውጤት መሰረት ተሰልፈው ስለመጫወታቸው የሚያረጋግጥ ድንገተኛ ምርመራ ማድረጉንም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የምርመራ ስራው በሌሎች ክለቦች ላይ እንደሚቀጥልና ውጤቱም በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ገልጿል።

በዘንድሮ የውድድር ዓመት ተግባራዊ በሆነው የኤም.አር.አይ እና አካላዊ የዕድሜ ተገቢነት ምርመራ ክለቦች ካቀረቧቸው 2 ሺህ 10 ተጫዋቾች መካከል 762ቱ ምርመራውን ማለፋቸው ይታወቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...