መነሻ ገጽ Uncategorized ​ፋሲል ከተማ በአዲስ አበባ ድል ቀንቶታል
Uncategorized

​ፋሲል ከተማ በአዲስ አበባ ድል ቀንቶታል

አጋራ
አጋራ

በ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከተማ ድል ቀንቶታል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም አዲስ አበባ ከተማን የገጠመው ፋሲል ኤዶም ኮድዞ በ6 እና 32ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ባስቆጠራቸው ግቦች 2 ለ 0 ረቷል።መከላከያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።

ሊጉ ነገ ቀጥሎ ሲውል አምስት ጨዋታዎች በክልል እና በአዲስ አበባ ይደረጋሉ።የሊጉ መሪ ደደቢት ወደ አርባምንጭ ተጉዞ አርባምንጭ ከተማን የሚገጥምበት ጨዋታ መሪነቱን ለማጠናከር እንደሚያግዘው ይጠበቃል።ከደደቢት ጋር በእኩል 17 ነጥብ በግብ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው አዳማ ከተማ በሊጉ ግርጌ ከሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር 9 ስአት ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም ይጫወታል። በተመሳሳይ 9 ስአት ላይ ጅማ አባ ቡና ከሲዳማ ቡና እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ጨዋታዎችን ያደርጋሉ።

ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ ቡና የተሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ነገ 11 ስአት ከ30 ላይ ይጀምራል።

ወልድያ ከተማ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናን በመጪው አርብ በመልካ ቆሌ ያስተናግዳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...