ድሬዳዋን ተቀላቅሎ የነበረው ሰለሞን ገብረመድህን ወደ ፋሲል ከተማ አመራ 

image

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ለመተሐራ ስኳር ለሰበታ ከተማ ለኢትዮጵያ ቡና እና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድኖች በመሀል ሜዳ ስፍራ ላይ እግር ኳስን በመጫወት ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ሰለሞን ገብረመድህን በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሎ ልምምዱን መስራት ከጀመረ በኃላ አሁን ደግሞ ከክለቡ ተለያይቶ የፕሪምየር ሊጉን ውድድር ዘንድሮ ወደ ተቀላቀለው ፋሲል ከተማ አምርቷል፡፡
በመሐል ሜዳ ጥሩ ተጨዋችነቱ የሚታወቀው ሰለሞን የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ቡድንን በአሰልጣኙ ዘላለም ሽፈራው ተፈልጎ በመግባቱ መደሰቱንና ለክለቡም ውጤት ማምጣት በእዚህ ዓመት ጥሩ ብቃቱን ለማሳየት መዘጋጀቱን በቅርቡ ለወጣው ሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን የሰጠ ቢሆንም ሰለሞን ምክንያቱን ባላወቀበት ሁኔታ ወደ ድሬዳዋ የገባበት ውሉ ለፌዴሬሽኑ ባለመግባቱ የቡድኑ ህጋዊ ተጨዋች ሳይሆን ቀርቷል፡፡
አሁን ግን በአሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ ወደሚመራው ፋሲል ከተማ በማምራት እና በመፈረም የቡድኑ ተጨዋች ሆኗል፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook