መነሻ ገጽ Uncategorized ​የኘሪሜየር ሊጉ የመጀመሪያ ዙር ማጠናቀቂያጨዋታዎች ነገና ከነገ በስቲያ ይካሄዳሉ
Uncategorized

​የኘሪሜየር ሊጉ የመጀመሪያ ዙር ማጠናቀቂያጨዋታዎች ነገና ከነገ በስቲያ ይካሄዳሉ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር 15 ሳምንት ማጠናቀቂያ ጨዋታዎች ነገና ከነገ በስቲያ ቀጥለው ይደረጋሉ።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች የሚስተናገዱ ሲሆን፥ 9 ሰዓት ላይ በፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ከወልድያ ከተማ ይጫወታሉ።

11 ሰዓት ከ30 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ።በሳምንቱ አጋማሽ ንግድ ባንክ በቡና 5ለ2 የተሸነፈ ሲሆን፥ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር አቻ መለያየቱ ይታወሳል።

የነገው ጨዋታ ለሁለቱም ወሳኝ ሲሆን፥ ጊዮርጊስ ደረጃውን አስጠብቆ ለመዝለቅ ንግድ ባንክ ደረጃውን ለማሻሻል የሚጫወቱ ይሆናል። እሁድ ስድስት ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ይስተናገዳሉ።

በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያ ሲዳማ ቡናን 9 ሰዓት ላይ ሲያስተናግድ፥ ክልል ላይ ጅማ አባቡና ከድሬዳዋ፣ አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና፤ ፋሲል ከተማ ከአዳማ ከተማ በተመሳሳይ 9 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

10 ሰዓት ላይ ደግሞ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ደደቢት ከወላይታ ዲቻ ይገናኛሉ።

11ሰዓት 30 ላይ ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀዋሳ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።

ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ በእኩል 26 ነጥብ በጎል ልዩነት 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ላይ ሆነው ይመሩታል።

ደደቢትና ሲዳማ ቡና በእኩል በ24 ነጥብ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና በ23 ነጥብ ተከታዮቹን ስፍራዎች ይዘዋል።

እስካሁን በፕሪምየርሊጉ ሁለት ጨዋታዎችን ያሸነፈው አዲስ አበባ ከተማ በ9 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፥ ጅማ አባቡና

በ10 እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ በ11 ነጥቦች ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኙ ክለቦች ናቸው።ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን የደደቢቱ ጌታነህ ከበደ በ10 ጎል ሲመራ፥ አዳነ ግርማ በ6 ጎሎች ይከተለዋል።

የደረጃ ሰንጠረዥና የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎችን ደረጃ ይመልከቱ

ደረጃ ሰንጠረዥ



ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...