ደደቢት ከ ቅ/ጊዮርጊስ
በመጀመሪያው ዙር የሊጉ ምርጥ ቡድን በወጣቶች እና ልምድ ባለቸው ስብስብ ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ለዋንጫ ሲጫዎት የነበረው ደደቢት በሁለተኛው ዙር ለበርካቶች ጥያቄን የሚፈጥር የውጤት መንሸራተት ካጋጠማቸው ቡድኖች ቀዳሚው ቦታ የሰማያዊ ሰርጓጆቹ ደደቢቶች ነው፡፡በአንፃሩ የዛሬው ተጋጣሚያቸው
ቅ/ጊዮርጊስ በሁለተኛው ዙር በርካታ ነጥቦችን ከሰበሰቡ ቡድኖች ቀዳሚ ነው፡፡ ባስመዘገቡት ውጤት ሁለት መልክ ይዘው የሚገናኙት ደደቢት እና ቅ/ጊዮርጊስ ዛሬ 11:00 የሚያደርጉት ጨዋታ ፉክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል፡፡
ባለፈው ሳምንት አዲግራት ላይ በወልዋሎ አዲግራት ዩ/ቲ ሽንፈት ያስተናገዱት ደደቢቶች ዛሬ ወደ ዋንጫው የሚያደርገውን ግስጋሴ ለማሳመር ወደ ሜዳ የሚገባውን ቅ/ጊዮርጊስ ሊፈትኑት እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡በዝናባማው የሸገር የምሽቱ የአዮር ፀባይ ሁኔታ ወልዲያን 3-1 የረቱት ፈረሰኞቹ ዛሬም ለላቀ ድል ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል፡፡ከዋንጫ ፉክክሩ በየሳምንቱ እየራቁ የመጡት ደደቢቶች የዛሬው ውጤትም ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ይመለሳቸዋል ተብሎ አይጠበቅም፡፡
የደደቢቶቹ አስራት መገርሳና ኩዌኩ አንዶህ በፈረሰኞቹ ቤት አዳነ ግርማ በቅጣት ከጨዋታው ውጭ ሲሆኑ የቅ/ጊዮርጊሶቹ አማራ ማሌ፡ሳላዲን ሰይድና፡ሪቻርድ አፒያ በጉዳት ለቡድናቸው ግልጋሎትን የማይሰጡ ሲሆን በሰማያዊዎቹ ቤት ከጉዳት ጋር የተያያ ዜና የለም፡፡ሁለቱም ቡድኖች በዚህ ጨዋታ ኳስን ተቆጣጥረው ወደ ግብ ለመድረስ የሚያደርጉት ሂደት የሚጠበቅ ሲሆን ቡድኖቹ አማካኝ ላይ በርከት ያሉ ተጨዋቾችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉም ይጠበቃል፡፡በዚህ ጨዋታ የመሀል ሜዳውን ሚዛን በአመዛኙ የሚወስድ ቡድን የተሻለ ግብ የማስቆጠር ዕድል ይኖረዋል፡፡የጨዋታው እንቅስቃሴ ከወቅታዊ የከተማዋ የአየር ሁኔታ ጋር በተገናኘ መልኩን ሊቀይር እንደሚችል ይገመታል፡፡ፈረሰኞቹ ባለፈው ሳምንት ከወልዲያ ከተማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ኳስን መስርቶ ከመጫዎት ይልቅ በፈጣን ተሻጋሪ ኳሶች ምርጫቸውን አድርገው ግቦችንም ያገኙ እንደመሆኑ ዛሬ ግን ሁለቱም ቡድኖች ሊሞክሩት እንደሚችሉም ይጠበቃል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በመጀመሪያው ዙር ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት ባደረጉት ጨዋታ ያለግብ አቻ ነበር የተለያዩት፡፡
ይህን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ፌደራል ዳኛ ሀይለየሱስ ባዘዘው ይመራዋል፡፡
ድሬድዋ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
በቀጣይ ዓመት በኘሪሚዮር ሊጉ ለመቆየት ጠንካራ ፉክክር የሚስተዋልበት በታችኛው የሊጉ ግርጌ በወራጂ ቀጠናውና አፋፉ ላይ የሚገኙት ድሬድዋና ኤሌክትሪክ ድሬድዋ ላይ በ9:00 የሚያደርጉት ጨዋታ ሌላኛው ትኩረትን ካገኙ ጨዋታዎች አንዱ ነው፡፡ዓመቱን በሙሉ ከወገብ በታች ወራጂ ቀጠና በመግባትና በመውጣት እያሳለፉ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች በመገባደድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኘሪሚዮር ሊግ የትኛው የሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ይዘው ያጠናቅቃሉ የሚለው አሁንም የሚጠበቅ ቢሆንም፡ድሬድዋና ኤሌክትሪክ እርስበርሳቸው ላለመውረድ በሚያደርጉት ፉክክር ዛሬ የሚያስመዘግቡበት ውጤት ለሁለቱም ወሳኝነቱ የጎላ ነው፡፡
በሁለተኛው ዙር በሜዳው ጥሩ ውጤትን ማስመዝገብ የቻሉት ድሬዎች ባለፈው ሳምንት ሀዋሳ ላይ በሲዳማ ቡና ሽንፈት ቢያስተናግዱም በዚህ ጨዋታ ወላይታ ድቻን አዲስ አበባ ላይ 2-0 ለረቱት ኤሌክትሪኮች እንደማይበገሩ የሚጠበቅ ቢሆንም ተጋጣሚቸው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወራጅ ቀጠና ወጥተው በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ እስከ 11 ከፍ የሚሉበትንና ላለመውረድ የሚያደርጉትን ጥረት ለማጠናከር አጋጣሚውን ለመጠቀም በሚያደርጉት ትንቅንቅ ጠንካራ ፉክክር ይጠበቃል፡፡በኤሌክትሪክ በኩል በቅርብ ሳምንታት ከሜዳቸው ሲዎጡ በትልቁ ከመቸገራቸውም ባለፈ የሚያስተናግዷቸው ግቦች 5,6 መሆናቸውን ስንመለከት ዛሬስ የተከላካይ ክፍሉ ምን ሊሆን እንደሚችል ሜዳ ላይ እንመለከታለን፡፡
በዚህ ጨዋታ ሄኖክ ካሳሁን በጉዳት በእንግዳዎቹ ቤት ወደ ድሬድዋ ያልተጓዙ ሲሆን በባለሜዳዎቹ ድሬዎች በኩል የቅጣትም ሆነ የጉዳት ዜና ስለመኖሩ አልተነገረም፡፡
ጨዋታው ጥንቃቄ የሚደረግበት ቢሆንም ግብ ለማግኘት በሚደረግ ሂደት የጨዋታው እንቅስቃሴ ክፍት ሊሆን እንደሚችልም ይገመታል፡፡ሁለቱም ቡድኖች ከጨዋታው ውጤት እንደመፈለጋቸው ነጥብ የሚጋሩ ከሆነም ለሌሎች የቅርብ ተፎካካሪዎቻቸው መልካም አጋጣሚን መፍጠሩም አይቀሬ ነው፡፡በደብዛዛው የኢትዮ ኤሌክትሪክ ቤት ጎልቶ የወጣው አልሀሰን ካሉሻ ዛሬም የሚጠበቅና ለድሬድዋ የተከላካይ ክፍል ፈተና ሁኖ እንደሚውል ይታሰባል፡፡
ጨዋታውን ኢ/ል ዳኛ በላይ ታደሰ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡


