ዛሬ በተደረገው የቶታል ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ሐ 4ኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል አምርቶ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸነፈ

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ጨዋታው እንደተጀመረ የመጀመሪያወቹን 6ደቂቃዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኳስን ተቆጣጥረው በመጫወት የበላይነት ነበራቸው
ሆኖም በ7ኛው ደቂቃ ቪታዎች ጎል አስቆጥረው መሪነቱን ይዘውነበር ከጎሉ መቆጠር ቡሃላ ቪታዎች ጫና ፈጥረው ለመጫወት ችለዋል በተደጋጋሚም ወደግብ መድረስ ችለው ነበር፡፡
በ26ኛው ደቂቃ ፍሬዘር ካሳ በፈጸመው ጥፋት ፍጹም ቅጣት ምት ሲሰጡ ለፍሬዘር ካሳም ቢጫ ካርድ አሳይተውታል፡፡
ቪታወችም ፍጹም ቅጣት ምቱን ወደጎልነት በመቀየር 2ለ0 በመምራት ጫናቸውን አጠናክረው ሲቀጥሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በበኩላቸወ በተደጋጋሚ ጊዜ ኳስ ሲበላሽባቸው እና እርስበርስ መግባባት ሲያቅታቸው ተስተውለዋል
በሁላታኛው አጋማሽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር እና ጫና በመፍጠር ጎል ለማስቆጠር ሲሞክሩ ተስተውለዋል በተለይ አዳነን በበሃይሉ ቀይረው ካስገቡ እና አብዱል ከሪም ኒኪማን ወደመስመር አስገብተው ከተጫወቱ ቡሃላ በተደጋጋሚ ወደጎል መድረስ ችለው ነበር ፡፡ በ65ኛው ደቂቃ ሳላዲን ሰኢድ የግብ ጠባቂውን መውጣት ተመልክቶ ወደግብ የመታው ኳስ ወደግብነት ተቀይሮ የቅዱስ ጊዮርጊስን ተስፋ አላምልሞት ነበር ከጎሉ መቆጠር ቡሃላ ሁለቱም ክለቦች በኳስ ቁጥጥሩ እና ወደጎል በተደጋጋሚ በመድረሱ እረገድ የተመጣጠኑ ነበሩ፡፡
በዚሁም ጨዋታው በቪታ 2-1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
አስተያየት ይስጡ