መነሻ ገጽ አፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለት የሀገራችን ሜዳዎች ፍቃድ አግኝተዋል
አፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግካፍኮንፌድሬሽን ካፕዋልያዎቹዜናዎች

ሁለት የሀገራችን ሜዳዎች ፍቃድ አግኝተዋል

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ ፣ ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አህጉራዊ ውድድራቸውን የሚያደርጉበት ሜዳ ታወቀ።

ሲዳማ ቡና የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ በመሆኑ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ሲወክል ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ከሲዳማ ቡና ጋር ጨዋታውን የሚያደርገው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ደግሞ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሀገራችንን ሁለቱም በመወከል ይካፈላሉ። ካፍ በቀጣዩ አመት ሀገራትም ሆኑ ክለቦች ውድድሮቻቸውን የሚያደርጉበትን ስታዲየም ይፋ ሲያደርግ ሁለት የሀገራችን ሜዳዎች ውድድሮች እንዲያደርጉ መመረጥ ችለዋል።

ካፍ እንዳሳወቀው ከሆነ የአዲስ አበባው አበበ ቢቂላ ስታዲየም እና የድሬዳዋ ስታዲየም የተመረጡት ሁለቱ ሜዳዎች ሲሆን በዚህ መሠረት በቅድመ ማጣሪያ በአህጉራዊ ውድድር ላይ ከነሐሴ 29/2018 ጀምሮ መካፈል የሚጀምሩት ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ምርጫቸውን አበበ ቢቂላ ስታዲየምን ምርጫቸው ማድረጋቸውን ሲያሳውቁ በመስከረም ወር ደግሞ ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የማጣሪያ መርሀግብር የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በድሬዳዋ ስታዲየም መጫወት እንደሚችል ታውቋል ይህም ኢትዮጵያ ከአምስት አመታት የሰው ሀገር መንከራተት በኋላ በደጋፊዎቿ ፊት የነጥብ ጨዋታዋን ታከናውናለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...