መነሻ ገጽ ዜናዎች 38ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

38ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

አጋራ
አጋራ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

  1. ነገሌ አርሲ : ክለቡ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ባደረገው የ38 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የነገሌ አርሲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
    1 አብርሃም ከተማ
    2 ናትናኤል ሰለሞን
    3ሚኪያስ ፍቅሬ
    4ሮኅቦት ሰላሎ
    5 ትንሳዬ ኑራ
    በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
  2. አደም አባስ (ተጫዋች-ባህር ዳር ከተማ): ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ጋር ባደረገው የ38 ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በ90+7 ኛ ደቂቃ ጎል ካገባ በኋላ ከማልያው ስር በለበሰው ልብስ ሃይማኖታዊ መልእክት ስለማስተላለፉ ሪፖርት ተደርጎበታል። በመሆኑም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ 9.2(ተራ ቁጥር 6) መሰረት ተጫዋቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 / አስር ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ ወስኗል።
  3. ፍሬዘር ካሳ (ተጫዋች መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ነገሌ አርሲ ጋር ጋር ባደረገው የ38 ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በ59ኛ ደቂቃ ጎል ካገባ በኋላ ሃይማኖታዊ መልእክት ስለማስተላለፉ ሪፖርት ተደርጎበታል። በመሆኑም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ 9.2(ተራ ቁጥር 6) መሰረት ተጫዋቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 3ዐዐዐ /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 1ዐዐዐዐ /አስር ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡
    ማጠቃለያ
    በሊጉ ተሳታፊ የነበሩት 20 ክለቦች በውድድር አመቱ ባደረጓቸው 38 ጨዋታዎች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ በክፍል 5 አንቀጽ 26(1-4) በተደነገገው የነጥብ አሰጣጥ ባጡት ውጤት እና በዚሁ ደንብ ክፍል 5 አንቀጽ 27( 1 ) እና ክፍል 7 አንቀጽ 31 ( 1 ) በተደነገጉት ድንጋጌዎች መሰረት ፦
  4. በሊጉ ከፍተኛውን ነጥብ ያስቆጠረው ሲዳማ ቡና (68 ነጥብና 20 ግብ ክፍያ) የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን እንዲሁም ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ሻምፒዮን ሊግ ውድድር ላይ ተካፋይ እንዲሆን
  5. ከ17 እስከ 2ዐኛ ደረጃ የተቀመጡት አራት ቡድኖች ምድረ ገነት ሽረ (42 ነጥብ እና -8 ግብ ክፍያ 17ኛ ደረጃ)፣ ድሬደዋ ከተማ (42 ነጥብና -14 ግብ ክፍያ 18ኛ ደረጃ )፣ መቐለ 70 እንደርታ (40 ነጥብና -12 ግብ ክፍያ 19ኛ ደረጃ ) እና አርባምንጭ ከተማ (35 ነጥብና 16 ግብ ክፍያ 20ኛ ደረጃ ) ከሊጉ እንዲወርዱ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...