የሰርቪያዊው አሰልጣኝ ማረፊያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወይንስ ሲ ኤፍ ሴፋክሲያን።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ከታዩ ውጤታማ አሰልጣኞች አሰልጣኞች መካከል አንዱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ዘለግ ያሉ አመታትን በማሳለፍ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ለአምስት ጊዜያት ማንሳት የቻሉት ሰርቪያዊው አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊቲን ሚቾ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ባሻገር እንደ ታንዛኒያው ያንጋ አፍሪካ ፣ የደቡብ አፍሪካውን ኦርላንዶ ፓይሬትስ እና የግብፁን ዛማሌክ ፣ የሱዳኖቹን አልሂላል ኤል ሜሪክን ጨምሮ 11 ክለብ እና ከዩጎዝላቪያ ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን አንስቶ እንደ ሩዋንዳ ፣ ዩጋንዳ ፣ ዛምቢያ እና ሊቪያ አይነት ብሔራዊ ቡድኖች ማሰልጠን የቻሉት የ56 አመቱ አሰልጣኝ ከአልጄሪያው ክለብ ኢ ኤስ ስቲፍ ጋር ከተለያዩ በኋሃላ ላለፉት ወራት የቀድሞውን ክለባቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአማካሪነት ሲያገለግሉ መቆታቸው ይታወሳል።
በቀጣዩ የውድድር ዘመን ለሦስተኛ ጊዜ ኢትዮጵያዊውን ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመያዝ ቀዳሚ ተመራጭ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አሰልጣኝ ከቱኒዚያው ክለብ ሲ ኤፍ ሴፋክሲያን ጋር ድርድር መጀመራቸው የአፍሪካን ሶከር ድረገፅ ዘገባ ያመላክታል። ከክለብ አፍሪካ ኢ ኤስ ቱኒዝ በመቀጠል ሦስተኛ ደረጃን ይዞ የ2025/26 የቱኒዝያ ፕሪምየር ሊግየን ያጠናቀቀው ክለቡ በአህጉሪቷ ያላቸውን ልምድ በማሰብ ቀጣዩ አሰልጣኙ ለማድረግ በጥረት ላይ ስለመሆናቸው ጠቁሞ ንግግር እንደጀመሩ ገልፆ ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሸነፍ አሰልጣኙ አድርጎ ይሾማል የሚለው ጉዳይም በቀጣይ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ