መነሻ ገጽ ኢትዮጵያን በውጪ ጋቶች ፓኖም አዲስ ክለብ ተቀላቀለ
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ጋቶች ፓኖም አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

አጋራ
አጋራ

ግዙፉ አማካይ ጋቶች ፓኖም ወደ ኩዌቱ ክለብ አምርቷል።

በኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ውድድር ላይ ጋምቤላን ወክሎ በ2003 የውድድር ዘመን ዝዋይ ባቱ ላይ ባሳየው ድንቅ ብቃት በኢትዮጵያ ቡና ዕይታ ውስጥ ገብቶ ከእግር ኳስ ማህበረሰቡ ጋር መተዋወቅ የቻለው ግዙፉ የተከላካይ አማካይ ቦታ ተጫዋቹ ጋቶች ፓኖም ከሳውዲው ክለብ አል አራቢ ወደ በኩዌት ፕሪምየር ሊግ ስድስተኛ ሆኖ ወደቋጨው አል ፋሀል ክለብ በይፋ አምርቷል።

በሀገር ውስጥ ከኢትዮጵያ ቡና በኋላ ለመቐለ 70 እንደርታ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ መድን የተጫወተው የወቅቱ የዋልያዎቹ አምበል ወደ ሩሲያው ክለብ አንዚ ማካቻካላ ለግብፆቹ ኤልጉና እና ሀራስ ኤልሁዳድ ለሳውዲው አል አንዋር ለኢራቆቹ ኒው ሮዝ እና አልናጃፍ ከተጫወተ በኋላ የተጠናቀቀውን አመት ደግሞ በድጋሚ ወደ ሳውዲ በመመለስ በአል አራቢ ቆይታ ማድረግ የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ኩዌት በማምራት አል ፋሀልን በይፋ መቀላቀሉ ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...