መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና ከሦስት ክለቦች ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሱት አሰልጣኝ ቡናማዎቹን ሊረከቡ ነው
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ከሦስት ክለቦች ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሱት አሰልጣኝ ቡናማዎቹን ሊረከቡ ነው

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ከሦስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ያነሱት አንጋፋው አሠልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌ ኢትዮጲያ ቡናን ለመረከብ በቃል ደረጃ ከስምምነት ደርሰዋል።

ከኢትዮጲያ መድን ጋር ያላቸው ውላቸው ያለቀው አሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌ ከፋሲል ከነማ የቦርድ አካላት ጋር በነበራቸው ውይይት 15 ሚሊዮን የፊርማ ሊሰጣቸው ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻም ግን ማረፊያቸውን ቡናማዎቹ ቤት ለማድረግ ከጫፍ ደርሰዋል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ቡናን አሰልጥነው ያለፉት አሰልጣኙ ከኢትዮጲያ ቡና አመራሮች ጋር ባለፉት ጥቂት ቀናት ውይይት ያደረጉ ሲሆን የክለቡ አመራርም ፍላጎታቸው የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ማንሳት እንደሆነ መስማማታቸው ይፋ ሆኗል።

ለጊዜው በሁለቱ አካላት መካከል ያለው ስምምነት በመርህ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን በቀጣዮቹ ጊዜያቶች የወረቀት ጉዳዮች የተካተቱበት ስምምነት እንደሚኖር ይጠበቃል። አሠልጣኙ በኢትዮጲያ ቡና አመራሮች በኩል ከፍተኛ የዝውውር በጀት እንደሚመደብላቸው እና በቂ ድጋፍ እንደሚያገኙም ለማወቅ ተችሏል።

አሠልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ ከዚህ ቀደም የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ከጅማ አባጅፋር ፣ መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጲያ መድን ጋር ማሳካታቸው የሚታወስ ሲሆን ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መቻል ፣ ሲዳማ ቡና እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠናቸው ይታወሳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...