ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዉድድር ላይ ተሳታፊ የሆነዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎችን ተሸንፎ ከዉድድሩ ዉጪ ሆኗል።
የሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታዉን ከግብፁ አሊ አህሊ ጋር ያደረገዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4-0 በሆነ ዉጤት ተሸንፎ በድምር 7-0 በሆነ ዉጤት ከአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዉድድር ዉጪ ሆኗል።
ፈረሰኞቹ ባሳለፍነዉ እሁድ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከግብፁ አሊ አህሊ ጋር አድርገዉ 3-0 በሆነ ዉጤት መሸነፋቸዉ የሚታወስ ነዉ።