ከሐዋሳ ከተማ ፍሬማ ጊዜ በኋላ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሰበታ ከተማዎችን መቀላቀል ችሎ የነበረው እስራኤል እሸቱ የአሰልጣኝ ደግ አረገ ይግዛውን ስብስብ ወልቂጤ ከተማ መቀላቀሉ ተሰምቷል ።
የሰበታ ከተማ ቡድን በዚህ ሳምንት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አራፊ መሆኑን ተከትሎ የቡድን አባላቱ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን ሀትሪክ ስፖርት ባገኘችው መረጃ እስራኤል ከ ቡድኑ ጋር አለመመለሱን ለማወቅ ችለናል ።
እስራኤል እሸቱ በወልቂጤ ቤት የክትፎዎቹን የአጥቂ ክፍል በማጠናከር ጉልህ ድርሻን ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል ።