መነሻ ገጽ ዜናዎች ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና 1-1 ሲለያዩ፣ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ መድንም በተመሳሳይ 1-1 አቻ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1-1 ሀድያ ሆሳዕና

በመጀመሪያው አጋማሽ ብዙም ማራኪ ያልነበረው ጨዋታ በ11ኛው ደቂቃ ሀድያ ሆሳዕና ቀዳሚ ሆኖዋል። አሸናፊ ኤልያስ ያቀበለውን ኳስ ቢንያም ጌታቸው በግንባሩ በመግጨት የመጀመሪያዋን ጎል ማስቆጠር ችሏል። የመጀመሪያው አጋማሽም ሀድያ ሆሳዕና 1-0 በመምራት ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በኳስ ቁጥጥር የተሻለ ብልጫ የወሰደ ቢሆንም ሀድያ ሆሳዕና ወደ ግብ በመቅረብ የተሻሉ አጋጣሚዎችን ፈጥራለች።በ90ኛው ደቂቃ የሀድያ ሆሳዕና ተጫዋች ቶሎሳ ንጉሥ በእጁ ኳሱን በመንካቱ የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት አስቻለው ታመነ ወደ ጎልነት በመቀየር ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከሽንፈት ማዳን ችሏል።በቀሪው የጨዋታ ጊዜ ሌላ ጎል ሳይታይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሀድያ ሆሳዕና ነጥብ በመጋራት ጨዋታውን በ1-1 አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ፋሲል ከነማ 1-1 ኢትዮጵያ መድን

በመጀመሪያው አጋማሽ ፋሲል ከነማ የጨዋታውን ብልጫ በመውሰድ ወደ ግብ በመቅረብ የተሻለ ብቃት አሳይቷል። ኢትዮጵያ መድን በአንፃሩ የተዳከመ አቀራረብ ያሳየ ሲሆን አደገኛ የጎል ሙከራ ማድረግ አልቻለም። የመጀመሪያው አጋማሽም ያለ ጎል በ0-0 ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽ የሁለቱም ቡድኖች የተሻለ ፉክክር ያደረጉበት ጨዋታ በ60ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ መድን መሪነቱን ወስዷል። ሳሙኤል ሳሊሶ ያገኘውን እድል በአግባቡ በመጠቀም መድንን ወደ መሪነት አሸጋግሯል።ፋሲል ከነማ ጨዋታውን ለማመጣጠን ጫና ያደረገ ሲሆን በ80ኛው ደቂቃ
አብዱ መሐመድ በጀሮም ኦዲ በአብዱ መሐመድ ላይ በፈፀመው ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ወደ ጎልነት በመቀየር ፋሲል ከነማን አቻ አድርጓል።ከአቻነት ጎሉ በኋላ ፋሲል ከነማ ተጨማሪ ጫና በመፍጠር የመሪነት ጎል ለማግባት ቢጥርም የተሳካ ሙከራ ማድረግ አልቻለም። በመጨረሻም ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ መድን በ1-1 አቻ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀላባ ከነማኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ኢትዮጵያ ቡና እና ሀላባ ከተማ አንድ አቻ ተለያዩ

በአቤኔዘር አበበ ኢትዮጵያ ቡና ከሀላባ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በ1-1 ነጥብ መጋራት ተጠናቋል።...

ሀዲያ ሆሳዕናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ እና ሀድያ ሆሳዕና ተለያዩ

ሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኙ ደካማ ውጤት በማስመዝገባቸው ከክለቡ ጋር ተለያዩ ሀዲያ ሆሳዕና እግር...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የ6ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች 1. በረከት ካሌብ (መቻል) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ...

ባህርዳር ከተማወልዋሎዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ባህርዳር ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩ. ነጥብ ተጋርተዋል

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም. የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ...