መነሻ ገጽ ሀላባ ከነማ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀላባ ከተማ አንድ አቻ ተለያዩ
ሀላባ ከነማኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ኢትዮጵያ ቡና እና ሀላባ ከተማ አንድ አቻ ተለያዩ

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

ኢትዮጵያ ቡና ከሀላባ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በ1-1 ነጥብ መጋራት ተጠናቋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተመልካች የሚስብ እንቅስቃሴ ሳያሳዩ የ45 ደቂቃዎችን አጠናቀዋል። በሁለቱም በኩል ግብ ጠባቂዎችን የሚፈትን ሙከራ ሳይደረግ የመጀመሪያው አጋማሽ 0-0 ተጠናቋል።
ከዕረፍት መልስ በኋላ ግን ሁለቱም ቡድኖች የተሻለ እንቅስቃሴ በማሳየት የተሻለ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና የጨዋታ ብልጫውን ወስዶ ነበር።ኢትዮጵያ ቡና በ49ኛው ደቂቃ ዘላለም አባቴ አመቻችቶ ያቀበላትን ኳስ ኮስታይባ ምቦኑዩምዋሚ በግባሩ በመግጨት ኳሱን መረብ ላይ አሳርፎ ቡድኑን መሪ አድርጎ ነበር።የቡና መሪነት ግን ለረጅም ጊዜ አልቆየም። በ55ኛው ደቂቃ ረጅብ ሚፍታህ በሀላባ ከተማ ተጫዋች እስራኤል ሾጎለ ላይ በፈጸመው ጥፋት የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሽመክት ጉግሳ ወደ ግብነት በመቀየር ሀላባ ከተማን አቻ አድርጓል።በቀሪው የጨዋታ ጊዜ ሌላ ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው በ1-1 ውጤት ተጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀዲያ ሆሳዕናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ እና ሀድያ ሆሳዕና ተለያዩ

ሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኙ ደካማ ውጤት በማስመዝገባቸው ከክለቡ ጋር ተለያዩ ሀዲያ ሆሳዕና እግር...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የ6ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች 1. በረከት ካሌብ (መቻል) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ...

ባህርዳር ከተማወልዋሎዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ባህርዳር ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩ. ነጥብ ተጋርተዋል

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም. የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ...