በአቤኔዘር አበበ
በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን የመጨረሻ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከነገሌ አርሲ ጋር ተገናኝቶ ሲዳማ ቡና 2-0 በሆነ ውጤት ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል።

በመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ፉክክር የበዛበት ጨዋታ ቢደረግም፣ ጥራት ያላቸው የግብ ዕድሎች ብዙም አልተፈጠሩም። ሁለቱም ግብ ጠባቂዎችም በተግባር የሚፈትናቸው አጋጣሚዎች ሳይኖሩ የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ጎል ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ነገሌ አርሲ ጨዋታውን በመቆጣጠር የተሻለ አፈጻጸም ቢያሳይም፣ ሲዳማ ቡና ያገኘችውን የግብ ዕድል በአግባቡ ተጠቅማ የጨዋታውን ሚዛን ለመቀየር ችላለች።በ83ኛው ደቂቃ ብርሃኑ በቀሌ በጥሩ ሁኔታ ያመቻቸውን ኳስ ኮስ መስፍን ታፈሰ በሚያስደንቅ አጨራረስ ወደ መረብ በመላክ ሲዳማ ቡናን መሪ አድርጓል።ጨዋታው ወደ መጨረሻው ደቂቃዎች ሲገባ በ89ኛው ደቂቃ አቤል ያለው በሚያምር ግብ የሲዳማ ቡናን ሁለተኛ ጎል በማስቆጠር የቡድኑን ድል አረጋግጧል።
ነገሌ አርሲ 0-2 ሲዳማ ቡና
አስተያየት ይስጡ