መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዲሲፕሊን ውሳኔ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ስጥቷል።

በ አስራ አምስተኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዘጠኝ ጎሎች ከመረብ አርፈዋል ። በዚህ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሀያ ሶስት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 389 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል።

በ አስራ አምስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች የ ሀድያ ሆሳዕናው ተስፋዬ አለባቸው የቀይ ካርድ የተመለከተ ብቸኛው ተጫዋቾች ናቸው ።

የዲሲፕሊን ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ

1. ተስፋዬ አለባቸው (ሀድያ ሆሳዕና) :- እሁድ የካቲት 28 2013 ዓ ም ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ 15 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ላይ በ90+3 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ወስኗል።

2. ሀድያ ሆሳዕና ከ ባህር ዳር ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ አይዛክ ኢሴንዴ ፣ መድሃኔ ብርሀኔ ፣ ተስፋዬ አለባቸው ፣ ዱላ ሙላቱ እና በድጋሚ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ ተስፋዬ አለባቸው መመልከታቸውን ተከትሎ ብር 5,000 ( አምስት ሺህ ብር ) የገንዘብ መቀጮ ተላልፎባቸዋል ።

ሀድያ ሆሳዕና ከዚህ በተጨማሪም አይሳክ ኢሴንዴ በአምስት ጨዋታዎች የቢጫ ካርድ የተመለከተ በመሆኑ ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት አንድ ጨዋታ እንዲታገድ እና
በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል ።

የወልቂጤ ከተማው ተስፋዬ ነጋሽ እንዲሁም የፋሲል ከተማው ሀብታሙ ተከሰተ በሊጉ አምስት ጨዋታዎች የቢጫ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ በተመሳሳይ አንድ ጨዋታ እንዲታገዱ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ወስኗል ።

የሁለተኛ አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜን በሰዓት ለማስጀመር የተሰጠ ማሳሰቢያ !

ባህርዳር ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና ክለብ ባደረገው የ15ኛ ሳምንት ግጥሚያ ወቅት የባህርዳር ከተማ ተጫዋቾች በሁለተኛው 45 ደቂቃ ጨዋታው መጀመርከሚገባው ሰዓት 2 ደቂቃ ዘግይተው ወደ ሜዳ መግባታቸውን የዕለቱ የጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት አድርገዋል ። ይህም ሁኔታ በ ባህር ዳር ከተማም ሆነ በሌሎች ክለቦችወደ ፊት መደገም የማይገባው ተግባር ነው።

በመሆኑም ከለቦች የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ማጠናቀቂያ ፊሽካ ከተነፋበት ጊዜ ጀምሮ የሚሰጣቸውን የዕረፍት ጊዜ 12ቱን ደቂቃ መልበሻ ክፍል ውስጥ በማረፍና የተቀረውን 3 ደቂቃ ወደ መጫወቻ ሜዳ በመውጣት ለሁለተኛው 45 ደቂቃ ጨዋታ ጅማሬ ዝግጁ መሆን ይኖርባቸዋል።

የሁለተኛው 45 ደቂቃ መጀመር ከሚገባው ሰዓት ዘግይቶ የተጀመረ ከሆነ ለመዘግየቱ ምክኒያት በሆነው ቡድን ላይ በውድድር ደንብ ምዕራፍ 1 አንቀፅ 13 ተራ ቁጥር 16 ና 17 መሰረት ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ የውድድር አመራርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ያሳስባል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...