By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለክላውድ አውት ኩባንያ የእንደራሴነት ሹመት ሰጠ……
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንዜናዎች

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለክላውድ አውት ኩባንያ የእንደራሴነት ሹመት ሰጠ……

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

“ከክላውድ አውት ኩባንያ ብዙ ውጤታማ የሆነ ሥራ እንጠብቃለን። ቢሮክራሲው እንዳያስቸግረውም የቻልነውን ሁሉ እንጥራለን”
አቶ ባህሩ ጥላሁን
/የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ/

“አሰልጣኞች፣ዳኞችና ታዳጊዎች ስልጠና እንዲያገኙ የእኔ ሥራ ድልድይ መፍጠር ነው”
አቶ ዮሀንስ ዘውዱ
/የክላውድ አውት ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ/

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከክላውድ አውት ኩባንያ ብዙ ውጤታማ ሥራ እንደሚጠብቅ ለዚህም ቢሮክራሲው እንዳያስቸግረው የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

- ማሰታውቂያ -

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከክላውድ አውት ኩባንያ ጋር አብሮ ለመስራት ስለተስማማበት ስምምነት የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁንና የኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሀንስ ዘውዱ/ ጆኒ ቬጋስ / በጋራ በፌዴሬሽኑ ጽ/ ቤት በሰጡት መግለጫ የሁለቱ ተቋማት ስምምነት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ትርጉም ያለው እንደሆነ አስረድተዋል።

“የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የማይደርስባቸው አድማሶች አሉ። ሁሉንም ቦታ መድረስ አንችልም ወይም ሁሉንም የምናውቅ የተዋጣልን አይደለንም ስለዚህ አብረውን የሚሠሩ አጋሮች ያስፈልጉናል” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ” ዮሐንስ ዘውዱ በክላውድ አውት ኩባንያው ከትላልቅ ካምፓኒዎች ጋር ያደረጋቸው ግንኙነቶች አሉ። እነዚህን ካምፓኒዎች ለማግኘት እጅግ በጣም ከባድ እንደሆነ እናውቃለን… እሱ ደግሞ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ለሀገሩ አስተዋጽኦ ማድረግ ይፈልጋል በስምምነቱም ተደስተናል” ሲሉ አስረድተዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ባህሩ “አቶ ዮሀንስ ጊዜውን የሚያሳልፈው ኮከብ ከሆኑ ተጫዋቾች ጋር እንደሆነ ይታወቃል እና እኛ የምንፈልገው ነገር አለ እሱም ለሀገሩ መሥራት የሚፈልገው ነገር አለ ስለዚህ አብረን መሄዱን መርጠናል። ከዕቅዳችን አንዱ ዱባይ በሚገኘው ቢሮው አማካይነት በታዳጊ ስልጠና ዘርፍ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ያለውን ጠንካራ የሆነ መንግሥታዊ ትስስር በእግርኳሱም ለማምጣት ምቹ ሁኔታ ይፈጥርልናል ብለን እናምናለንሲሉ አብራርተዋል።

“ከቀድሞዎቹ ፍራንሲስኮ ቶቲ፣ ባካሪ ሳኛና አሁን ደግሞ እነ ሳካን ጨምሮ በርካታ ኮከቦችን በቀላሉ የሚያገኝ ሰው ነው። ካምፓኒውም በዛ ደረጃ የሚሠራ ነው። ከተቋሙ ብዙ ውጤታማ የሆነ ሥራ እንጠብቃለን። ቢሮክራሲው እንዳያስቸግረውም የቻልነውን ሁሉ እንጥራለን” ያሉት አቶ ባህሩ ” ከካፍና ፊፋ ጋር ያለን ግንኙነት ብቻውን በቂ አይደለም ዮሐንስ ዘውዱ ታላላቅ የእግርኳስ ሰዎች እና ክለቦች ጋር አለም አቀፍ ሥራዎችን እንደሚሠራ ይታወቃል። ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይዞት የመጣው ሥራ ቀላል አይደለም” ሲሉ ስምምነቱን አወድሰዋል።

በስምምነቱ መሰረት አቶ ዮሀንስና ተቋማቸው ልክ እንደ ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመሆን ከተለያዩ የአለማችን ታላላቅ ሊጎች ጋር እና የስፖርት ትጥቅ አምራቾች ጋርም ሆነ ሌሎች ፌዴሬሽኖች ጋር በጋራ በመሆን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በመወከል ለኢትዮጵያ እግርኳስ የሚጠቅመውን እንዲያመጡ
ተቋማዊ ውክልና እንደተሰጠው ተናግረዋል።

የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሀንስ ዘውዱ በበኩላቸው “የእኔ ሥራዬ ድልድይ መፍጠር ነው በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና የውጭ ሊጎች መሃል መልካም ግንኙነት በመፍጠር የኢትዮጵያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ወደ ላይ አውጥቶ ዕውቅና ለመስጠት፣ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ፣ ለሀገራችን አሰልጣኞችና ዳኞች የስልጠና ግንኙነቶችን ለማመቻቸትና ከውጪው ዓለም ጋር በምንፈጥረው ግንኙነት ታዳጊዎችን የማፍራት ሥራ ለመስራት ነው። ክላውድ አውት ፌዴሬሽኑ ወደ ውጪ ጉዞ ሲያደርግ ከሆቴሎች ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠርና ወጪውን ለመቀነስ ዋና አላማው እድርጎ ይንቀሳቀሳል” ሲል ተናግረዋል። አቶ ዮሀንስ ከዚህ ቀደም የተጫዋቾችን የዕረፍት ጊዜ እጅግ ምቹ በሆነ ሁኔታ ያዘጋጁ እንደነበር በማስረዳት አሁን እነሮሜሎ ሉካኩ ከቀድሞዎቹ ደግሞ ደግሞ ባካሪ ሳኛን የመሳሰሉ ተጫዋቾች ከካምፓኒያቸው ጋር እንደሚሠሩ ጠቁመዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ባህሩ በሁለቱ ወገኖች መሃል ለፈጠረው የግንኙነት መስመር ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒን አመስግነዋል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቀጣዩ ዙር መቀላቀል ሳይችል ቀርቷል።
Next Article የመጀመሪያው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከደቂቃዎች በኋላ ይደረጋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግኢትዮጵያ ቡናወልዋሎ

የኢትዮጲያ ቡናና የወልዋሎ አዲግራት ጨዋታ ተራዘመ

hatricksport team By hatricksport team 7 years ago
ኢትዮጵያ ቡና አራት ተጨዋቾቹን ቀጥቷል
የጨዋታ ዘገባ | ሙጅብ ቃሲም ሀትሪክ በሰራበት ጨዋታ ሀይቆቹ ድል ቀንቷቸዋል !
ሰበታ ከተማ በይፋ ተጫዋች አሰፈረመ
ፋሲል ከነማ ከዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር እንደሚጫወት ተረጋግጧል !!
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?