የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለታው ሙገር ሲሚንቶ ሊፈርስ?ሁኔታው አሳዛኝ ነው

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለታው ሙገር ሲሚንቶ ሊፈርስ?
ሁኔታው አሳዛኝ ነው

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ሲነሳ ለሀገሪቱ ስፖርት እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካደረጉት ክለቦች መካከል አንዱ የነበረውና በተለይ ደግሞ ታዳጊና
ወጣት  ተጨዋቾችን ከስር ኮትኩቶ በማሳደግ ይታወቅና ሀገርን በሚጠቅም ደረጃም ልጆቹን ለከፍተኛ እውቅና የሚያበቃው ድንቁና ተወዳጁ የሙገር እግር ኳስ ቡድንን ድርጅቱ ሊያፈርሰው
መቃረቡን የሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ
ከክለቡ አካባቢ ያገኘውን መረጃ በጭምጭምታ መልኩ ሊሰማ ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ምርጥና ተደናቂ የነበሩትን እግር ኳስ ተጨዋቾች እንደ እነ

image

ሳላህዲን ሰይድን አህመድ ሰይድን አራፋት ሰይድን አንዱዓለም ንጉሴ አቤጋን  እስክንድር አብዱላሚድን ወንድሜነህ ዘሪሁን ኦኬን ቢኒያም ሀብታሙ ኦሼን
አብዱልከሪም አባፎጊን ጄምባ ኤፍሬም ቀሬን ሱራፌል ጌታቸውን ፍፁም ገብረማሪያምን ሁነኛው ዳምጤን ሚካሄል ጆርጅ እና ሌሎች በርካታ ተጨዋቾችን ያፈራው ይህ ክለብ ሊፈርስ መቃረቡ ሲሰማ እኛን ጨምሮ ብዙዎችን እያሳዘነም ይገኛል፡፡
የሙገር እግር ኳስ ቡድን ሊፈርስ የተቃረበው የወንዱም የሴቱም ሲሆን ምንአልባትም የተስፋ ቡድኑ ብቻ ሊኖር እንደሚችልም መረጃዎች እየወጡ ይገኛል፡፡  ያ ከሆነ ደግሞ ከእዚህ በፊት ፈርሶ የነበረውንና በወጣት ተጨዋቾች ብቻ  ይጓዝ የነበረውንና በኃላ ላይ የፈረሰውን ኪራይ ቤቶችን ያስታውሰናል፡፡  በሙገር ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘንላችሁ የምንመጣ ይሆናል

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook