የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታላቁ የደርቢ
ጨዋታ ነገ 10፡00 ሰዓት ላይ የሊጉን ዋንጫ ለ13 ጊዜ ባነሳው ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ዋንጫውን ለአንድ ጊዜ ባነሳው ኢትዮጵያ ቡና መካከል ይካሄዳል፤ የሁለቱ ክለቦች ተጠባቂ እና አጓጊም ጨዋታ በነገው እለት ሲከናውን በሁለቱም ቡድኖች ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች መካከል አንዱ በአንዱ መሸነፍን አጥብቀው የሚጠሉት ስለሆነ ግጥሚያው በየዓመቱም ከፍተኛ አትኩሮትን የሚስብም ሆኗል፤ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የነገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ባለሜዳውና ገቢውን የሚያገኘው ቡድን /ሁለቱም የራሳቸው የሆነ ሜዳ ባይኖራቸውም/ ኢትዮጵያ ቡና ሲሆን የሁለተኛው ዙር ላይ ሲገናኙ ደግሞ ገቢው የቅ/ጊዮርጊስ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና
————————————————————
ቅዱስ ጊዮርጊስ
የቅ/ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና የደርቢ ጨዋታ ሁሌም የሚጠበቀው ሁለቱ ክለቦች በፕሪምየር ሊግ ላይ ሲገናኙ ብቻ ሳይሆን በማናቸውም ጨዋታዎች ላይ ሲሆን በቀድሞ አባባል ለበረኪና ዋንጫ ቢጫወቱ እንኳን አንዱ አንዱን ለማሸነፍም ከፍተኛ ጥረትን የሚያደርጉም ይሆናል፤ የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች ከዋናው ቡድኖቻቸው ባሻገር በተስፋ ቡድን፣ በወጣት ቡድን በታዳጊ ቡድን እና በሴቶች ቡድንም ሲጫወቱ ያለው ፍልሚያም እንደዋናው ቡድኖቻቸው ሲሆን ሁለቱ ክለቦች የአንድ ከተማ ክለብ ከመሆናቸው አኳያ የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤት በመሆናቸውም በተራ ቋንቋም እርስ በእርስ የሚበሻሸቁም ስለሆነ ያ ሁሉ ተደማምሮበት ጨዋታው ከመድረሱ በፊትም ሆነ በኋላ ሁሌም መነጋገሪያ መሆናቸውን ቀጥለዋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ለሀገራችን ብሔራዊ ቡድን በርካታ ተጨዋቾችን ማለትም ከታችኛው ሊግ ተያይዘው ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ላይ በጥቂቱ የቅዱስ ጊዮርጊሶቹን፣ ሰለሞን መኮንን /ሉቼን/፣ ሙሉጌታ ከበደን /ወለዬው/፣ ገብረመድህን ኃይሌን፣ ጌቱ ከበደን /ሰላዩ ሬሳን/፣ ደሳለኝ ገብረጊዮርጊስን፣ ዳኛቸው ደምሴን /ዳኙ ገላግሌን/፣ ተስፋዬ ኦርጌቾን /ተምዘግዛጊው ሚሳኤል/፣ ሙሉዓለም ረጋሳን፣ አንተነህ ፈለቀ፣ አንዱዓለም ንጉሴ /አቤጋን/፣ ዳዊት መብራቱን /ገዳዳው/፣ ደጉ ደበበን፣ ሳላህዲን ሰይድን /ሳላ/፣ አዳነ ግርማን /ወፍጮ/ እና የመሳሰሉትንና የኢትዮጵያ ቡናዎቹንም ሙሉጌታ ወልደየስን /አቦሸማኔ/፣ ሚሊዮን በጋሻውን /የሞላ ውይይት/፣ መንግስቱ ቦጋለን፣ ፀጋዬ ፋንታሁንን /ፍሪጅ/፣ አስራት አዱኛን /ኤፍኤ/፤ ጥላሁን መንገሻ፤ ዮናስ፣ ካሳዬ አራጌ /ኢንጅነር/ አብዱራህማን አብዱራዛቅ /ናይጄሪያን/ አሰግድ ተስፋዬን /ጂረስ/፣ አንተነህ አላምረውን፣ ዮርዳኖስ አባይን /ቡሎ/፣ ዳዊት እስጢፋኖስን /ዳቪንቺ/፣ መስዑድ መሐመድን /አረብ/ የመሳሰሉት ተጨዋቾች ያሰየንና አሁንም እያሳየን ያለው የደርቢ ጨዋታ ወደፊትም ብዙዎቹን ያሳየናል ብለን እንጠብቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለቱ ቡድኖች የእስከዛሬ የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ለ34 ጊዜ የተካሄደ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ ለ18 ጊዜ ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና 6 ጊዜ ባለድል ሆኗል፤ 10 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፤ የሁለቱ ቡድኖችን የነገው ግጥሚያ ማን በበላይነት ያጠናቅቃል፤ ጨዋታው በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲጠናቀቅ የሀትሪክ ስፖርት ድህረ- ገፅ ምኞቷ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ ውድድር ለ20ኛ ጊዜ እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን በተደረጉት የሰባት ሳምንታት ጨዋታዎችም ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ደደቢትና አዳማ ከተማ በእኩል 14 ነጥብ ላይ ሆነው እንደቅደም ተከተላቸው በግብ ክፍያ በመበላለጥ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ሊይዙ ችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ተኛ ሳምንት የዛሬ ውጤቶች
– የደረጃ ሰንጠረዥ
-ጎል አግቢዎች ደረጃ
————————————————————
ቅዳሜ ታህሳስ 22 ቀን 2009
————————————————-
ደደቢት
2-1
ኢትዮጵያ ንግድባንክ
19′ 45+1′ ጌታነህ ከበደ | 63′ አዲሱ ሰይፉ
ፋሲል ከተማ
0-0
ኢትዮ. ኤሌክትሪክ
ወላይታድቻ
1-0
ወልድያ
34’መሳይ አንጪሶ (ፍ.ቅ.ም)
ሲዳማ ቡና
3-1
ሀዋሳ ከተማ
9′ በረከት አዲሱ 61′ ፍፁም ተፈሪ 82′ አዲስ
ግደይ| 90′ አረፋት ጃኮ
አዳማ ከተማ
1-0
ጅማ አባ ቡና
77’ዳዊት ሁጤሳ
ድሬዳዋ ከተማ
0-1
አርባምንጭ ከ
90+2 አማኑኤል ጎበና
መከላከያ
2-1
አዲስ አበባ ከተማ
40’ሳሙኤል ታዬ47’ምንይሉ ወንድሙ |1’ሀይሉ እሸቱ
——————————————————–
እሁድ ታህሳስ 23 ቀን 2009
10 ሰዓት
ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
——————————————————–
የደረጃ ሰንጠረዥ
# ክለብ ተጫ ልዩ ነጥብ
1 ደደቢት 8 7 17
2 አዳማ ከተማ 8 5 17
3 ቅዱስ ጊዮርጊስ 7 9 14
4 ሲዳማ ቡና 8 2 14
5 ፋሲል ከተማ 7 3 12
6 አርባምንጭ ከተማ 8 1 12
7 ወላይታ ድቻ 7 1 11
8 መከላከያ 7 -1 11
9 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 7 -1 8
10 ድሬዳዋ ከተማ 8 -3 8
11 ኢትዮጵያ ቡና 7 -3 7
12 ወልድያ 8 -3 7
13 ጅማ አባ ቡና 8 -5 6
14 አዲስ አበባ ከተማ 7 -3 5
15 ኢትዮ ኤሌክትሪክ 8 -4 5
16 ሀዋሳ ከተማ 7 -5 5
——————————————————–
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች
ደረጃ ተጨዋች ጎል
1 ጌታነህ ከበደ 8
2 አዳነ ግርማ 4
3 ሳላዲን ሰኢድ 3
4 ሙጂብ ቃሲም 3
5 ገብረሚካኤል ያዕቆብ 3
6 ፍቃዱ አለሙ 3
7 ያቡን ዊልያም 3
8 አማኑኤል ጎበና 2
9 ፍጹም ተፈሪ 2
10 ማራኪ ወርቁ 2
11 ቴዎድሮስ በቀለ 2
12 ዳዊት እስጢፋኖስ 2
13 ፒተር ኑዋዲኬ 2
14 ፍሬው ሰለሞን 2
15 ወንድሜነህ ዘሪሁን 2


አስተያየት ይስጡ