መነሻ ገጽ Uncategorized የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ሉሲዎቹ በረሂማ ዘርጋ ሶስት ግቦችና በሎዛ አበራ አንድ ግብ አዘጋጇን ኡጋንዳ በማሸነፍ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኑ
Uncategorized

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ሉሲዎቹ በረሂማ ዘርጋ ሶስት ግቦችና በሎዛ አበራ አንድ ግብ አዘጋጇን ኡጋንዳ በማሸነፍ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኑ

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ሉሲዎቹ በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የመጀመሪያው የሴካፋ ውድድር ላይ ተካፋይ በመሆን ሲወዳደሩ ቢቆዩም እንደተጠበቁት ግን ዋንጫውን ማንሳት አልቻሉም፤ የሉሲዎቹ የእዚህ ውድድር ተሳትፎም አዘጋጇን ሀገር ኡጋንዳን 4-1 በማሸነፍ ሊጠናቀቅ ችሏል፤ ለሉሲዎቹ ዛሬ በተደረገው ጨዋታ የድሉን ግቦች ያስቆጠሩት ሀትሪክ በመስራት ረሂማ ዘርጋ እና ሎዛ አበራ ደግሞ ቀሪውን በማስቆጠር ነው፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮ ተሳትፎአቸው በምድባቸውም ባደረጉት ጨዋታ ሩዋንዳን ሎዛ አበራ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ግቦችና መስከረም ካንኮ ባገባችው አንድ ግብ 3ለ2 አሸንፈው ከታንዛኒያ ጋር ደግሞ ያለግብ አቻ የተለያዩ ሲሆን ለፍፃሜ ለማለፍ እሁድ ዕለት ከኬኒያ አቻቸው ጋር ባደረጉት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ደግሞ ሎዛ አበራ በድጋሚ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ግቦች 3ለ2 በሆነ ውጤት መሸነፋቸው በአፍሪካ አህጉር በእግር ኳሱ ካላቸው ጅማሮና ጥንካሬ አንፃር እንደዚሁም በቡዙዎች ከሚሰጣቸው ከፍተኛ ግምት አንፃር የሴካፋን ዋንጫ የማግኘት ህልማቸውና ተስፋቸው ሊያከትም መቻሉ ሁሉንም ሊያሳዝን መቻሉ ይታወሳል፡፡ 

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በኬኒያ በግማሸ ፍፃሜ ተሸንፈው ከወደቁ በኋላ የመጨረሻ የሚባለውን ጨዋታቸውን ለደረጃ በዛሬው እለት ከአዘጋጇ አገር ኡጋንዳ ጋርም አድርገው 4-1 ማሸነፋቸው ከፍፃሜው የኬኒያ እና የታንዛኒያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወሳኝ ጨዋታ በኋላ የነሐስ ሜዳሊያ የሚያሸልማቸው ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ለደረጃ የገጠመውንና ያሸነፈውን የኡጋንዳ የሴቶች ብሄራዊ ቡድንን ከእዚህ ቀደም ማለትም ከ15 ዓመታት በፊት በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ላይ ተገናኝተን የነበረ ሲሆን ያኔም የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በሜዳው 2ለ0 በማሸነፍና ካምፓላ ላይ ደግሞ 2ለ2 ከተለያየ በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ተሳትፎው ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን ቡድኑ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት በውድድሩ ላይ ስላደረጋቸው ፍልሚያዎች የጨዋታ ፊልሞችን ፈልጎ ይዞ በመምጣት በጨዋታው ዙሪያ ስለነበረን ጠንካራ እና ደካማ ጎን በመነጋገር ባለሙያዎችን በመጋበዝ ከእዚህ ቀደም የነበሩትን መሸፋፈኖች ወደኋላ አስቀርተን ያለምንም መሸፋፈን ጥልቅ ውይይት ሊደረግበት ይገባል፤ ያን ስናደርግም እግር ኳሱ ላይ ለውጥ ይመጣል፡፡

ሉሲዎቹ በሰላም ወደ ሀገራችሁ ግቡ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...