መነሻ ገጽ Uncategorized ​የኡጋንዳ የእግር ኳስ ቡድን ይዛ ትጓዝ የነበረች ጀልባ ከ30 ሰዎች ጋር ሰጠመች
Uncategorized

​የኡጋንዳ የእግር ኳስ ቡድን ይዛ ትጓዝ የነበረች ጀልባ ከ30 ሰዎች ጋር ሰጠመች

አጋራ
አጋራ


የኡጋንዳ የእግር ኳስ ቡድንንና ደጋፊዎችን የጫነች ጀልባ በአልበርት ኃይቅ ስትጓዝ ከ30 ሰዎች ጋር የመስመጥ አደጋ ገጠማት፡፡

ጀልባዋ ከአቅም በላይ ጭና በመጓዟ በአልበርት ሀይቅ ውስጥ መስመጧን የኡጋንዳ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በወቅቱ ጀልባዋ 45 ሰዎችን ጭና በመጓዟ እና ሚዛኗ ወደ አንድ ወገን በማጋደሏ ልትገለበጥ መቻሏን ነው ፖሊስ የገለፀው፡፡ አደጋው ከተከሰተ በኋላ 15 ሰዎችን በህይወት ማዳን መቻሉን የገለፀው ፖሊስ፣9 አስክሬን ደግሞ ከሀይቁ ወስጥ ማውጣት ማቻሉ ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል፡፡

የስፖርተኞቹ ቡድን በገና በአል እለት ከሌላ አቻ የእግር ኳስ ቡድን ጋር ሊገጥም ይጓዝ እንደነበር ተገልጿል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...