የኡጋንዳው ክለብ ተጋባዥ የሆነበት11ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ቅዳሜ ይጀመራል

image

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ በስፖርቱ ዘርፍ ለሚያካሂዳቸው የልማት ፕሮግራሞች ራሱን በገቢ እንዲችል እና አቅሙን ለማጎልበት፣ የተሳታፊ ክለቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከርና እንደዚሁም ደግሞ ቡድኖቹም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከመግባታቸው በፊት የእራሳቸውን አቋም ለመለካት እንዲችሉ በየዓመቱ የሚያካሂደው የክልሉ የሲቲ ካፕ ዋንጫ ውድድር ዘንድሮም ከመስከረም 28 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን የሚካሄድ ሲሆን የውድድሩንም መርሐ ግብር የሚገልፀው የዕጣ ማውጣት ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሆቴል የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶችና የስፖርቱ አካላቶች በተገኙበት ተካሂዶ ድልድሉ ወጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው ይኸው የክልሉ ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓትም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭትን ያገኘ ሲሆን በእዚህም መሰረት
ዕጣውን በማውጣት በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት በተጨዋችነትም በአሰልጣኝነትም ከፍተኛ ስራ ሰርተው ካለፉት እና አሁንም ድረስ በሙያው ላይ የሚገኙት ኢንስትራክትር ሰውነት ቢሻው፣ አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ፣ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እና የአሴጋ ፕሮጀክት መስራች አሰግድ ተስፋዬ ናቸው፤ በእዚህም መስረት ዛሬ ባወጡት ዕጣ መሰረት ኢንስትራክትር ሰውነት ቢሻው በምድብ አንድ የተደለደለውን የቀድሞ ቡድናቸውን ኢትዮ-ኤሌክትሪክ እና በምድብ ሁለት የተደለደለውን ኢትዮ ንግድ ባንክን ዕጣ ሲያወጡ አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ ደግሞ ተጋባዥ ክለብ የሆነውን የኡጋንዳውን ኬሲሲኤ በምድብ አንድ ላይ እንዲቀመጥና አሁን በቴክኒካል ዳይሪክተርነት እየመሩት ያለውን ደደቢትን በምድብ ሁለት እንዲደለደል በዕጣ ሲያወጡ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ ደግሞ ባለፈው ዓመት ያሰለጠነውን መከላከያን በምድብ አንድ ላይ እና ሌላው ተጋባዥ ክለብን አዳማ ከተማን በምድብ ሁለት እንዲደለደል ዕጣ አውጥቷል፤ በመጨረሻ ደግሞ የዕጣ ማውጣት እድሉ የተሰጠው አሰግድ ተስፋዬ ደግሞ በምድብ አንድ ላይ ከእዚህ ቀደም የተጫወተበትን ቅዱስ ጊዮርጊስን በምድብ አንድ ላይ እንዲቀመጥ ሲያደርግ ዘንድሮ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው የአዲስ አበባ ከተማ ቡድን ደግሞ በምድብ ሁለት ላይ እንዲቀመጥ አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ካፕ ውድድር በእዚሁም መሰረት በምድብ አንድ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ኬሲሲኤ፣ መከላከያ እና ቅ/ጊዮርጊስን ሲያፋልም በምድብ ሁለት ደግሞ ኢት. ንግድ ባንክን፣ ደደቢትን፣ አዳማ ከተማን እና አዲስ አበባ ከተማን የሚያገኝ ይሆናል፤ የመክፈቻው ጨዋታ ቅዳሜ ሲጀመርም ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር እንደዚሁም ደግሞ ኬሲሲኤ ከመከላከያ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፤ በነጋታው እሁድ ደግሞ ኢትዮ. ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር እንደዚሁም ደደቢት ከአዳማ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ዋንጫን በእስከዛሬው የውድድር ተሳትፎው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለ4 ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚው ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ለሶስት ጊዜ በማግኘት ይከተላል፤ ኤሌክትሪክ ለሁለት ጊዜ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአንድ ጊዜ በተሳትፎው አሸናፊ ሊሆኑበት ችለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ካፕ ውድድር ዕጣ ዛሬ ሲወጣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻህን ጨምሮ ድንቁ የሀገራችን አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬም በስፍራው በተጋባዥነት ተገኝተዋል፡፡
የኡጋንዳው ቡድን ተጋባዥ የሆነበትጡጥበእዚህ አመት በ8 ክለቦች መካከል የሚያካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ በእዚህ ውድድር ላይ እንደማይሳተፍ በማሳወቁ በምትኩ ከክልል ክለቦች መካከል አንድ ተጋባዥ ቡድን ተካቶት የሚጫወት ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ከመስከረም 28 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ በውድድሩ ተካፋይ የሚሆኑት ቡድኖች የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኤሌክትሪክ፣ ደደቢት፣ መከላከያ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቡድኖች ሲሆኑ በተጋባዥነት ደግሞ የአዳማ ከነማ እግር ኳስ ክለብ እንደዓምናው ሁሉ ሲካፈል ሌላኛው አንድ ቡድን ደግሞ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በሚወስነው መሰረት ከጅማ አባቡና እና ከወልዲያ ከተማ ክለቦች መካከል አንዳቸው እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የሲቲ ዋንጫ መጀመርን በማስመልከት የቡድኖች የእጣ ማውጣት ስነ-ስርአት በዛሬው እለት የሚከናወንም ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ዋንጫን በእስከዛሬው የውድድር ተሳትፎው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለ4 ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ለሶስት ጊዜ ኤሌክትሪክ ለሁለት ጊዜ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአንድ ጊዜ በተሳትፎው አሸናፊ ሊሆኑበት ችለዋል፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook