የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተራዘመ

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተራዘመ

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተራዘመ

 11ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ እንደገለፀው ውድድሩ የሚጀመረመርበት ጊዜ እና የተራዘመበትን ምክንያትበቀጣይ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።ዛሬ ይጀመራል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባ ዋንጫ በሁለት ምድብ ስምንት ክለቦች ይሳተፉበታል።የዘንድሮው ውድድር ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ ከውጭ ሀገር የዩጋንዳው ኬሲሲኤ ክለብ በተጋባዥነት የሚሳተፍ ይሆናል።ከአዲስ አበባ ክለቦች በተጨማሪ አዳማ ከተማ የሚሳተፍ ሲሆን ፕሪሚየር ሊጉን በአዲስ መልክ የተቀላቀለውና በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራው አዲስ አበባ ከተማም ተሳታፊ ይሆናል።

በምድብ አንድ

ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መከላከያ፣ የዩጋንዳው ኬሲሲኤ እና ኤሌክትሪክ ተደልድለዋል።

በምድብ ሁለት

ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዳማ እና አዲስ አበባ ከተማ ይገኛሉ።

ጨዋታዎቹ በአዲስ አበባ ስታዲየም ነው የሚደረጉት።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook