የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ቡድን ስራ አስኪያጁንና ሌሎች ሰራተኞቹን ስራ እንዲያቆሙ አዘዘ

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን  ዘንድሮ የተቀላቀለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ቡድን የክለቡን ስራ አስኪያጅ ጨምሮ ቴክኒካል ዳይሬክተሩን የቡድን መሪውንና የሂሳብ ሰራተኛውን በአስቸካይና ጥድፊያ በሆነ ድንገተኛ ውሳኔ ስራ እንዲያቆሙ አዟል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በአምስት ዓመታት የምስረታ ጊዜው ሊቀላቀል የቻለው ይኸው ክለብ ቡድኑን ለአራት ዓመታት የመሩትንና ከቡድኑ አሰልጣኝ እና አመራሮች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው ሲነገርላቸው የነበሩትን ስራ
አስኪያጁን አቶ እንዳለየሱስ አባተን እንደዚሁም ቴክኒካል ዳይሬክተሩን

image

አቶ አበራ ሀብቴን እና ሌሎቹ ሁለቱ የክለቡ ሰራተኞችን ከቦታቸው እንዲለቁ ከውሳኔ ላይ እንደደረሰ የሚነገረው በአዲስ የመዋቅር ለውጥ ሊጓዝ እንደሆነ እና ሌሎች ሰዎችንም በእነሱ ምትክ ለማምጣት እንደሆነ ቢነገርም  ቡድኑ ሊጉን ከተቀላቀለበት አጭር ጊዜ አንፃርና  ቡድኑ ዝግጅት ገና ሳይጀምርም ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግም ሊጀመር
እየተቃረበ ባለበት ሰዓት ያለምንም የሽግግር ጊዜያት እና ውይይት የተወሰነው ውሳኔ አነጋጋሪ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በጉዳዮ ዙሪያ በቀጣይነት የሚመለከታቸውን አካላት አናግረን ሰፊ ዘገባዎችን ይዘንላችሁ የምንመጣ ይሆናል፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook