የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ቀጣይ ጨዋታ እሁድ ዕለትም የተከናወነ ሲሆን በእለቱም ፍልሚያ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን 1-0 ለማሸነፍ ችሏል!!!

 

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ራሱን በገቢ ለማጠናከር እና የሚገባውንም ገቢ ለተለያዩ የልማት ስራዎቹ ለማዋል ያዘጋጀው የሲቲ ካፕ ሻምፒዮና ዘንድሮም ለ11ኛ ጊዜ ከቅዳሜ ጥቅምት 12 ቀን አንስቶ በመከናወን ላይ ሲሆን ፍልሚያውም እስከ ጥቅምት 29 ቀን ድረስ በመካሄድም ፍፃሜውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ውድድር ቅዳሜ ሲጀመርም በተደረጉት ሁለት ጨዋታዎች መከላከያ ከጅማ አባቡና ጋር ተጫውቶ 0-0 ሲለያይ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከኤሌክትሪክ ጋር በመጫወት 4-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ለድል የበቃበትን ግብም አቡበከር ሳኒና ራምኬል ሎክ ሁለት ሁለት ሊያስቆጥሩ ችለዋል፡፡ ለኤሌክትሪክ ደግሞ ብቸኛዋን ግብ አዲስ ነጋሽ አስቆጥሯል፡፡

የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ቀጣይ ጨዋታ እሁድ ዕለትም የተከናወነ ሲሆን በእለቱም ፍልሚያ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን 1-0 ለማሸነፍ ችሏል፡፡ ለቡድኑ የድል ግቡንም ናይጄሪያዊው ፒተር ኑዋድንኬ ሊያስቆጥር በቅቷል፡፡ በሌላ ቀሪ ጨዋታ አዳማ ከተማ በተጠባባቂ ቡድኑ የገባውን ደደቢትን 3-0 አሸንፏል፡፡ ለአዳማ የድል ግቦቹን ጥላሁን ወልዴ ሱራፌል እና ፋሲካ አስፋው አስቆጥረዋል፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook