የትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አወዛጋቢ የነበሩትን አቶ ተክለወይኒ አሰፋን ከቦታቸው ማንሳቱን ተከትሎ ማንን ይተካሉ እሚለው ሀሳብ የስፖርቱን ቤተሰብ ሲያጠያይቅ የነበር ጉዳይ ነው ፡፡
እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በዛሬው እለት ትግራይ ክልልን እሚወክሉ ሁለት ስራ አስፈፃሚዎችን ይፋ ሊያደርግ ችሏል፡፡የደደቢት እግር ኳስ ቡድን መስራች እና ኘሬዝዳንት የነበሩትን ኮሎኔል ኣወል አብዱራሂምን እና የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ምክትል ዳይሬክትር የሆኑት እና በስፖርቱ መስክ በብዙ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ የቆዩትን ዶ/ር ወልደገብርኤል መዝገቦ ክልሉን ወክለው እንዲወዳደሩ የትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውክልና መስጠቱ አስታውቋል፡፡