መነሻ ገጽ Uncategorized “የቡድኔ ተጫዋቾችና ደጋፊው ያደረጉልኝ ውለታ በህይወት እንኳን የሚከፈል አይደለም”አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ
Uncategorized

“የቡድኔ ተጫዋቾችና ደጋፊው ያደረጉልኝ ውለታ በህይወት እንኳን የሚከፈል አይደለም”አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ

አጋራ
አጋራ

“ከእኔ ሕመም ይልቅ የቡድኔ
ውጤት ይበልጥ ያስጨንቀኛል”
አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ

15242017_1796465250613715_3980677247510988725_n.jpg

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከፍተኛ
ሊጉን በሻምፒዮንነት አጠናቅቆ ፕሪሚየር
ሊጉን የተቀላቀለው የፋሲል ከተማ
ክለብ በውጤቱና በደጋፊዎቹ (አፄዎቹ)
የፕሪሚየር ሊጉ ድምቀት ብቻ ሳይሆን
ክስተትም ሆነዋል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ
እንግዳ ቡድን ፋሲል ከተማ ከሀገሪቱ
ሀያላን ክለቦች ነጥብ ከመንጠቅ ባለፈ ድል
እያደረገም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት
ላይ ከሚገኙት ክለቦች መካከል አንዱ
ለመሆን ችሏል፡፡ ይህንን ቡድን ከታች
ጀምሮ በመያዝ ለውጤት ያበቃው ወጣቱ
አሰልጣኝ ዘ-ማሪያም ወ/ጊዮርጊስ ላለፉት
ሁለት ዓመታት በአንድ በኩል ከህመም
ጋር እየታገለ በሌላ በኩል ደግሞ ቡድኑን
ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በማስገባት የጎንደርና
አካባቢውን ህዝብ የረጅም ዓመታት ህልም
ለማሳካት ከፍተኛ ትግል ሲያደርግ ቆይቶ
ተሳክቶለታል፡፡ ይህ ለፋሲል ከተማዎች
ደማቅ ታሪክ ያፃፈው አሰልጣኝ በቅርቡ
ለሁለት ዓመታት ሲያሰቃየው ለነበረው
ህመም ፈውስ ለማግኘት ወደ ታይላንድ
ባንኮክ ተጉዞ ተመልሷል፡፡ የሀትሪክ ስፖርት
ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ
በላይ ወጣቱን አሰልጣኝ በህክምናውና
በቡድኑ አጠቃላይ ውጤት ዙሪያ ከዚህ
በታች ባለው መልኩ አነጋግሮታል፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን አሁን አሰልጣኝ ዘ-ማሪያም
የሚለው ስም በእግር ኳሱ በተለይ ከፋሲል ከተማ
ጋር በተያያዘ ከፍ ብሎ ሲጠራ እየተሰማ ነው
ለመሆኑ ዘ-ማሪያም የሚለውን ስም የፈጠረው
ፋሲል ከተማ ነው ወይስ ዘ-ማሪያም ፋሲል ከተማ
የሚለውን ስም ፈጠረ… የሚለው የጥያቄዬ
መጀመሪያ ቢሆንስ?
ዘ-ማሪያም፡- በጣም ቀላል ጥያቄ ነው፤
ምክንያቱም አሰልጣኝ ዘ-ማሪያም የታሪክ
ሀብታም፣ እግር ኳስ እንደ ሻይ በሱስ
የሚጠጣበት፣የእውነተኛ ደጋፊዎች ባለቤት
የሆነው ፋሲል ከተማን የመፍጠር አቅም
የለውም፡፡ ዘ-ማሪያም ፋሲል ከተማን ፈጠረ
ከሚለው ድፍረት የሚመስል ቃል ይልቅ
ታላቁ ፋሲል ከተማ ዘ-ማሪያም የሚባል
ትንሹን አሰልጣኝ ፈጠረ ቢባል ይመቸኛል፡
፡ የስልጠና ሀሁን የጀመርኩበት፣ ድል
ያጣጣምኩበት ፣ትልቅ የህዝብ ፍቅርም
ክብርም ያገኘሁት በፋሲል ከተማ በመሆኑ
ከላይ በገለፅኩት መሰረት ቢወስድልኝ ደስ
ይለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- በቅርቡ ለህክምና ወደ ባህር
ማዶ ተጉዘህ ነበር፤ የህመምህ መነሻና ህክምናህ
እንዴት ነበር?
ዘ-ማሪያም፡- ያጋጠመኝ ህመም
መጀመሪያይ ላይ ሀሞሮይድ ተብሎ ነበር፤
በኋላ ላይ ግን ፊስቱላ ነው የሚል ነገር
ነው የመጣው፡፡ ህመሙ ጠንከር ብሎ
ከያዘኝ ሁለት አመት አካባቢ ሞልቶታል፡
፡ የህመሙ ስሜት እየባሰ ሲመጣ በአገር
ቤት ህክምና ፈውስ ለማግኘት ሞክሬ ነበር፡
፡ ከሐበሻ መድሃኒት እስከ ዘመናዊ ህክምና
ብከታተልም ለውጥ ማምጣት አልቻልኩም፡
፡ ሐኪሞችም ብዙ ቢደክሙም ፈውስ ላገኝ
ባለመቻሌ “በአገር ቤት የመጨረሻ የተባለውን
ህክምና ነው እያደረግንልህ ያለነው፡፡ ከዚህ
የተሻለ ህክምና የለም፡፡ መዳን ከፈለክ የግድ
ወደ ውጪ ሄደህ መታከም አለብህ” የሚል
በአገር ቤት የመዳን ተስፋዬ ተሟጥጦ
ማለቁን በሚገልፅ መልኩ አረዱኝ፡፡ በዚህ
ወቅት ደግሞ የህመሙ ሁኔታ እየባሰ
መንቀሳቀስና መስራት ወደማልችልበት
ደረጃ እየተሸጋገረ መጣ፡፡ ነገሮች ለእኔነ
በጣም ፈታኝና ከባድ ቢሆኑብኝም በአንድ
በኩል ክለቤን ውጤታማ ለማድረግ በሌላ
በኩል ህመሜን እያስታመምኩ መስራቱን
ቀጠልኩ፡፡ መጨረሻ ላይ መራመድ ሁሉ
ያቃተኝ ደረጃ ላይ ደረስኩ፡፡ በዚህን ጊዜ
ነው ወደ ውጪ ሄዶ የመታከሙ አማራጭ
የማይቀርብለት ነገር የሆነው፡፡
ሀትሪክ፡- የውጪ ህክምናን ቀደም ሲል
በግልህ ለማሳካት አልሞከርክም? ወደ ቀድሞ
ጤንነትህ በቶሎ ለመመለስ?
ዘ-ማሪያም፡-እውነት ለመናገር ይሄ በእኔ
አቅም የሚሞከር ባለመሆኑ ያለፉትን ሁለት
አመታት ህመሜንና ስቃዬን በወስጤ አፍኜ
ነው ስሰራ የነበረው፡፡ ከነሐሴ-ነሐሴ ውድድር
ውስጥና ልምምድ ውስጥ ያለእረፍት
መቆየቴና በቂ ምህክምና አለማግኘቴ
ስቃዬን አብዝቶት ነበር፡፡ በተለይ ዶክተሮች
በተደጋጋሚ እረፍት አድርግ ቢሉኝም ከእኔ
ጤንነት ይልቅ የክለቤ ውጤት ይበልጣል
ብዬ አሻፈረኝ ማለቴ ህመሙን አክብዶብኛል፡
፡ በዚህ ውሳኔዬ የተማረሩ የህክምና
ባለሙያዎች “ወደ ውጪ ሄደህ በቂ ህክምና
ካልወሰድክ አደጋ ውስጥ ነህ፤ ስለዚህ
ቢያንስ ህክምና እስክታገኝ ስልጠናውን ትተህ
በሽታህን አስታምም፤ ከዚህ በኋላ ሃላፊነቱን
እኛ አንወስድም” ቢሉኝም ለክለቤ ቅድሚያ
ሠጥቼ እሺ ማለቱን አልመረጥኩም፡፡ በዚህ
ሁኔታ ውስጥ እያለሁ ያልታሰበ ነገር
ተፈጠረ፡፡ የቡድኑ ተጨዋቾች ለራሳቸው
ምንም ሳይኖራቸው “ከእኛ ደስታ ይልቀ
የአንተ ጤንነት ይበልጣል” ብለው ያገኙትን
የገንዘብ ሽልማት 830 ሺህ ብር ለህክምና
ሰጡኝኘ፡፡ በጣም ያልጠበቅኩት በመሆኑ ገና
ሃሳቡ ሲነሳ የህመሜ ስሜት ሁሉ ጠፋ፡
፡ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከ1.2 ሚሊዮን
ብር በላይ ነው በመባሉ የእኛ እና የቅዱስ
ጊዮርጊስ ጨዋታ የሜዳ ገቢ ተጨምሮበት
በቂ ህክምና ለማግኘት ወደ ታይላንድ ባንኮክ
በረርኩ፡፡
ሀትሪክ፡- በታላይላንድ የነበረው ህክምናስ?

wp-1481638398777
ዘ-ማሪያም፡- ህክምናው በጣም
የተዋጣለትና ትክክኛው ባለሙያዎች ጋር
ነበር የሄድኩት፡፡ መጀመሪያ የሄድኩት—-
የተባለ ሆስፒታል ነበር፡፡ እነሱ ከኛ ይልቅ
በዚህ በሽታ ልዩ ስፔሻሊስቶች ስላላቸው ወደ
ቡምበርግ ሆስፒታል ቀየርኩ፤ የተባለው
ሆስፒታል ሄጄ ስፔሻሊስቱ ሲያየኝ “ወደ
ትክክለኛው ቦታ ነው የመጣኸው፤ ለዚህ
በሽታ ትክክለኛው ሰው እኔ ነኝ፤ ህክምናህን
ተከታተል ትድናለህ” አለኝ፡፡ በዚህም
ስጓጓለት የነበረው ጤንነቴ ከእግዚያብሔር
ጋር እንደሚመለስ ተስፋ አድርጌ ህክምናዬን
ቀጠልኩኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ህክምናው እንደታሰበው ብዙ
ገንዘብ ጠይቋል?
ዘ-ማሪያም፡- በጣም የሚገርምህ
ለህክምና የያዝኩት 1.2 ሚሊየን ብር ነበር፤
ይሄ ገንዘብ ግን አልበቃኝም፤ ከራሴ 300
ሺህ ብር አካባቢ ጨምሬያለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- በቀጣይስ?
ዘ-ማሪያም፡-በቀጣይ አሁን በመጀመሪያ
ከእዛ ባመጣሁት የሀኪም ትዕዛዝ መሰረት
በአገር ቤት ባሉ ሀኪሞች ህክምናዬን
እከታተላለሁ፤ ለዳግም ቼክ አፕ ግን ከሶስት
ወር በኋላ ወደዚያው ተመልሼ እሄዳለሁ፡
፡ ተጨማሪ ህክምናዎችንና ምርመራዎችን
አደርጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- በውጪ በኩልስ በቀጣይ ምን
ለማድረግ አስበሃል? በምንድነው ህክምናህን
የምትከታተለው?
ዘ-ማሪያም፡- የጎንደር ከተማ ከንቲባ
ተመልሼ ለህክምና እንደምሄድ ነግሬ
ያቸዋለሁ፡፡ እኔ አቅም እንደሌለኝም ይታ
ወቃል፡፡ እሳቸው ግን “አይዞህ አታስብ፤ ወ
ጪውን እኛ እንሸፍንልሃለን” የሚል ተስፋ
ስለሰጡኝ በተስፋ ውስጥ ነኝ፡፡ ከክለቡ ጋር
ውል አለኝ፤ በስራ ላይ ስለታመምኩ በውሉ
መሰረትም ያግዙኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡

ሀትሪክ፡- የፋሲል ከተማ ተጨዋቾች “ከእኛ
ደስታ ይልቅ የአንተ ጤንነት” ብለው በሽልማት
ያገኙትን ገንዘብ ለአንተ መስጠታቸው ምን ስሜት
ፈጠረብህ?
ዘ-ማሪያም፡- እንደዚህ አይነቱ ነገር
ከዚህ በፊት ስለመደረጉ አላውቅም፤ እኔ
እስከማውቀው ድረስ ግን በኢትዮጵያ እግር
ኳስ ታሪክ እንደዚህ ዓይነት ነገር ተደርጎ
የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ “አሰልጣኛችን
እንደዚህ ሆኖ አናየውም፤ ለአመታት
ሲያስጨንቀው ከነበረው ህመም ደኖ
ማየት አለብን” ብለው በላባቸው ያገኙትን
ገንዘብ ምንም ነገር ሳይኖራቸው አንስተው
ለእኔ መስጠታቸው በህይወት ዘመኔ ሁሉ
የማልረሰው ብቻ ሳይሆን በህይወት እንኳን
የማይከፈል ትልቅ ውለታን ነው የዋሉልኝ፡
፡ በአጭሩ ህይወቴን ብሰጣቸው እንኳን
ውለታቸውን ከፍዬ አልጨርሰውም፡፡ ወደ
ውጭ ሄጄ መታከም አልችም ብዬ ተስፋ
በቆረጥኩበትና ነገሮች ሁሉ በጨለሙብኝ
ሰአት ፈጥነው የደረሱልኝ ልጄቼን ከልብ
ነው የማመሰግናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ከልጆቼ
ሌላ ጉዳዩ አሳስቧቸው ከጎኔ የሆኑትን
ሁሉ አመሰግናለሁ፤ አምላክ ውለታቸውን
ይክፈልልኝ ከማለት ውጪ ሌላ ምንም
አልልም፡፡
ሀትሪክ፡- በህመምህ ወቅት ከክለቡ
ደጋፊዎች በተለየ ሁኔታ አጋርነቱን ያሳየህ ወይም
ከውስጥህ በማይወጣ መልኩ ስሜቱን የገለፀ
የተለየ አጋጣሚ አለህ?
ዘ-ማሪያም፡- በእውነት የሆነውን
ለማመን በሚከብድ መልኩ ብዙዎች ከጎኔ
መሆናቸውን፤ በህመሜ ተፈውሼ ማየት
እንደሚፈልጉ የሚገልፁበት መንገድ
የሚከብድ ብቸ ሳይሆን ልብንም የሚነካ
ነበር፡፡ በተለይ ሀክምና ለማግኘት ወደ ባንኮክ
መሄዴ ከተረጋገጠ በኋላና ወደ ኤርፖርት
የሄድኩት ግማሹ ስሜቱን መቆጣጠር
አቅቶት እያለቀሰ፣ግማሹሽ አምላክን በፀሎት
እየተማፀነ አንዳንዱ ደግሞ እንደ ሃይማኖቱ
የእመበቴ ማሪያምንና የቅድስ ገብርኤልን
ምስል ይዘው፤ ሌሉቹ ደግሞ ፀበል እና
እምነት ይዘው ቀሪዎቹ ደግሞ የመልካም
ምኞት መግለጫ ፅሁፍ ያለባቸውን ባነሮች
ይዘው ነው የሸኙኝ ይሄ መቼም ከውስጤ
የማይጠፋና ስሜቴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ
ድረስ ልቤን የነካ አጋጣሚ ነበር፡፡ ከዚህ
ከገለፅኩልህ ውጪ ደግሞ አንድ የክለባችን
ደጋፊ ያደረገችው ነገር ደግሞ ህመሙ ከእኔ
አልፎ የከተማውን ነዋሪና በተለይ ደግም
የክለቡን ደጋፊዎች ምን ያህል እንዳስጨነቀ
የሚያሳይ ነው፤ ሰዎች ለአንተ ይሄን ያህል
ርቀት ሲሄዱ ማየት ለማመን የሚከብድ
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ያልካት ደጋፊ ምን የተለየ ነገር
ብታደርግ ነው…? አጫውተኝ እስኪ…?
ዘ-ማሪያም፡- አንድ ጊዜ ከህክምና
እንደተመለስኩ አንዲት ልጅ እኔ አላውቅም
ግን የክለባችን ደጋፊ ናት ልምምድ
ወደምንሰራበት ማነጋገር ፈልጌ ነው
ትላለች፤ ጥያቄው ያልተለመደ የሆነባቸውና
እኔ በመደበኛ ስራዬ ላይ መሆኔን
የተመለከቱ “ለምንድነው የፈለግከው እሱ
ስራ ላይ ነው ለእኛ ንገሪን ሲሏት “እባካችሁ
ፍቀዱልኝ ራሱን ነው ማናገር የምፈልገው”
ብላ ስታስጨንቃቸው “ትሂድና ታናግረው”
ብለዋት ወደ እኔ ጋር ትመጣለች ከዚያም
“በጣም ይቅርታ አንዴ ላናግርህ ፈልጌ
ነበር ትፈቀድልኛለህ?” ስትለኝ ጥያቄዋ
ያልጠበቅኩት በመሆኑ ቢያስደነግጠኝም
ጠጋ ብዬ እሺ ምን ነበር ስላት “…ስለት

አለብኝ… ለእሱ ነው የመጣሁት…” አለችኝ፡
፡ …ነገሩ ስላልገባኝ… በመገረም የምን ስለት
ነው…? አልኳት እሷም “ለቅዱስ ገብርኤል
ዘ-ማሪያም ጤንነቱ ተመልሶ ለውጥ አምቶ
ወደ ስራው አንዲመለስና ቡድናችንን
እንዲያሰለጥን…እሱን በጤናው ከመለስክልኝ
ከእሱ ጋር ሆነን ሰለቴን አስገባለሁ ብዬ
ተስያለሁ… አምላኬም ፀሎቴን ሰምቶ ቶሎ
ምላሹን ሰለሰጠኝ በገባሁት ቃል መሰረት
ከአንተ ጋር ሆኜ ስለቴን አስገባለሁ፤ ስለዚህ
አብረን ወደ ቤተክርስቲያን እንሂድ” ስ
ጠጋ ብዬ እሺ ምን ነበር ስላት “…ስለት
አለብኝ… ለእሱ ነው የመጣሁት…” አለችኝ፡
፡ …ነገሩ ስላልገባኝ… በመገረም የምን ስለት
ነው…? አልኳት እሷም “ለቅዱስ ገብርኤል
ዘ-ማሪያም ጤንነቱ ተመልሶ ለውጥ አምቶ
ወደ ስራው አንዲመለስና ቡድናችንን
እንዲያሰለጥን…እሱን በጤናው ከመለስክልኝ
ከእሱ ጋር ሆነን ሰለቴን አስገባለሁ ብዬ
ተስያለሁ… አምላኬም ፀሎቴን ሰምቶ ቶሎ
ምላሹን ሰለሰጠኝ በገባሁት ቃል መሰረት
ከአንተ ጋር ሆኜ ስለቴን አስገባለሁ፤ ስለዚህ
አብረን ወደ ቤተክርስቲያን እንሂድ” ስትለኝ
በቆምኩበት ደንዝዤ ቀረሁ የሰማሁት ሁሉ
ህልም መሰለኝ፤ አንድ አንዴ ይሄ የህመሜ
አጋጣሚ ለበጎ ነው እላለሁ፤ የህዝብ ፍቅር፣
ኢትዮጵያዊነት ማለት የት ድረስ እንደሆነ
በተግባር አይቼበታለሁ፡፡ ለዚህ ህዝብ
እንኳን እየታመሙ ማሰልጠን ህይወትህን
ብትሰጠውም ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም”
ሀትሪክ፡- እንዲህ ከምትለው ከፋሲል ከተማ
ጋር ያለህ ኮንትራት በያዝነው አመት ይጠናቀቃል
ይሄንን ተከትሎ ከሌላ ክለብ የሚያማልል ገንዘብ
ቀርቦልህ የአሰልጥንልን ጥያቄ ከመጣልህ ምላሽህ
ምን ሊሆን ነው?
ዘ-ማሪያም፡- በእርግጥ እንዳልከው
ከፋሲል ከተማ ጋር ያለኝ ከንትራት በዚህ
ዓመት ያልቃል፤ከክለቡ ገር የመቀጠሌ
አለመጠቀሌ ጉዳይ የሚወሰነው በእኔ ፍላጎት
ሳይሆን በክለቡ ነው፤ እኔ የክለቡን ውሳኔ
እከብራለሁ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ የፈለገ
ቁልል ብር ቢቀርብልኝ ፋሲል ከተማን ለቆ
ሌላ ክለብ ማሰልጠን ለእኔ በጣም ከባድ ብቻ
ሳይሆን ፈታኝ ነው። በተለይ በራሴ ፍላጎት
ፋሲልን ጥሎ መውጣት ውለታን የመብላት
ያህል ነው የሚሆንብኝ፤ ፋሲሎችን በገንዘብ
መቀየር ከባድ ነው፤ምክንያቱም ከገንዘብ
በላይ ናቸውና፡፡ እኔ እውነቱን ልንገርህ
የፋሲሎች ተከፍሎ የማያልቅ እዳ አለብኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ከዚህ አንፃር ታዲያ ፋሲል
ከተማን ብቻ አሰልጥነህ ልታቆም?
ዘ-ማሪያም፡- ለምን እስከ ህይወቴ
ፍፃሜ አይሆንም ፋሲሉችን እስከመጨረሻው
ባሰለጥናቸዉ በእኔ በኩል በጣም ደስተኛ ነኝ፤
ምክንያቱም ፋሲል ከተማ ለእኔ ብዙ ነገሬ
ነው፡፡ የስልጠና ሀሁን የጀመርኩበት፣ ብዙ
ስኬትና ተአምር እንዲሁም የህዝብ ፍቅር
ያየሁበት፣ እግር ኳስ የሻይ ያህል በሱስ
የሚጣጠበት ክለብ በመሆኑ በተይ በእኔ
ፍላጎት ከበክለቡ መለየትን አልመርጥም፡
፡ ነገሮች ግን የሚወሰኑት በእኔ ፍላጎት
ሳይሆን በክለቡ በመሆኑ የእነሱን ውሳኔ
እቀበላለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከተማ ፕሪምየር ሊጉን
እንደተቀላቀለ ከአንተ ጋር ባደረኩት ቃለ-ምልልስ ፋሲል ከተማ በወጣበት መሰላል
ተመልሶ የማይወርድ አዝናኝና ጥሩ ተፎካካሪ
የሆነ ቡድን እንደገነባህ ገልፀህልኝ ነበር፤ አሁን
እያስመዘገብከው ያለው ውጤትና የምትገኝበት
ደረጃ በእቅዳችሁ መሰረት ነው ማለት ነው?
ዘ-ማሪያም፡- ለእኔ አዎን በትክክል…!
ከፕሪምየር ሊጉ ውድድር በፊት በተካሄደው
የሲቲ ካፕ ውድድር ላይ የተሳተፍነው በ8 ቀን
ልምምድ ብቻ ነው፤ በውድድር ተንገላተን፣
በቂ እረፍት ሳናገኝ ነው ተመልሰን ውድድር
ውስጥ የገባነው፤ ይሄ ውሳኔ በጣም ከባድ
ነው። ሌሎች አሰልጣኞች ይሄን ከባድ
ውሳኔ ይወስናሉ ለማለት ይቸግረኛል፡፡ ሲቲ
ካፑ ላይ በነበረን ተሳትፎ በሶስት ጨዋታ
ተሸነፍፈን፤ በቂ ዝግጅትና እረፍት ሳናደረግ
ስለገባን ውጤቱን ጠብቀነዋል፤ ሽንፈቱንም
እንደ መልካም ነገር ነው የተቀበልነው፤
ምክንያቱም ከመነሻው ወደ ውድድር ስንገባ
እንደ መመሪያ የያዝነው በሽንፈታችን
መማርን ነው፤ እንዳሰብነውም ከሽንፈታችን
ተማርንብት። አሁን በቡድናችን ውጤት
ላይ እየታየ ያለው ከሲቲ ካፑ ትምህርት
ቤት የገበየነውን እውቀት ነው፤ አሁን
አጀማመራችን አምሯል፤ መጨረሻውን
ግን ይገልፃል ማለት አይደለም፡፡ እንደ
አጀማመራችን አጨራረሳችንንም ማስቀጠል
ነው ፍላጎታችን፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ
4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛላችሁ፤ አንድ ተስተካካይ
ጨዋታ እያላችሁ። ይህ ሁኔታ ስለዋንጫ ማሰብ
እንድትጀምሩ አድርጓችኋል?
ዘ-ማሪያም፡-ውድድሩር ገና 8ኛ ሳምንት
ነው ለእኛ፤ ቀሪ ብዙ ጨዋታዎች እያሉ ዛሬ
ስለ ዋንጫ ማሰብ ጠዋት ነው የሚሆነው።
ደረጃችን የዋንጫ ተፋላሚ ሊያስመስለን
ይችላል፤ እኔና የቡድኔ ተጨዋቾች ግን
ሁሉም የምናስበው ቀጣይ ጨዋታችን
ስለማሸነፍ ብቻ ነው፡፡ በየጊዜው ከፊትህ
የሚጠብቅህን ቀጣይ ጨዋታ እያሸነፍክ
መሄድ ነው ወደ ዋንጫው የሚያደርስህ
የሚል እምነት አለ በክለባችን፤ መሪ ብንሆን
እንኳን የምናስበው ቀጣዩን ጨዋታ ስለ
ማሸነፍ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ መንገድ
ሁሌም ከተጓዝክ መጨረሻህ ግቡ ዋንጫ ነው
የሚሆነው፡፡ ዋንጫ የሚጠላ ባይሆንም እኛ
ግን መመሪያችን ሁሌም ቀጣይ ጨዋታን
ማሸነፍ ብቻ ነው የሚሆነው ፡፡በዚህ መንገድ
ከተጓዝን ከምንፈልገው ዋንጫ ወይም ግብ
ላይ እንደርሳለን፡፡
ሀትሪክ፡- የፋሲል ከተማ ቡድን የፕሪምየር
ሊጉን ዘንድሮ ከተቀላቀልኩትም ሆነ ከነባር
ቡድኖች በበለጠ እንዴት በፍጥነት ፕሪምየር
ሊጉን ሊለምድ ቻለ…? ያለመቸገሩ ምክንያትስ
ምንድነው…?
ዘ-ማሪያም፡- በዋነኝት ልጆቼ ጋር
ያለው አዲስ ታሪክ የማሚፃፍ ቁርጠኝነትና
ተነሳሽነት ነው፡፡ የልጆቼና የደጋፊው
የማሸነፍ ስሜት ተመሳሳይ መሆኑም
ተረድቶኛል፡፡ ሱፐር ሊጉ ላይ አብረው
መቆየታቸው እያንዳንዱ ጨዋታ ለማሸነፍ
መጫወታቸውና በአንድነት ለውጤት
የመነሳታቸው ስሜት ይመሰለኛል፡፡ በጣም
የሚገርምህ ባለፈው አመት ለዳሽን ቢራ
የሚጫወቱ ልጆች እኛ ጋር አሉ፡፡ ስለቡድኑ
ወቀታዊ ሁኔታ ከእነዚህ ተጨዋቾች ጋር
ስናወራ ቱሙ ውስጥ ባለው የማሸነፍ ስሜት
በጣም ነው የሚገረሙት፡፡ ተጨዋቸች
ሲነግረኝ “ከዚህ በፊት ዳሽን ውስጥ ሆነን
ስንጫወት በተለይ ቡድኖች ጋር ስንጫወት
ቢያነስ እንኳን አቻ ብንወጣ ብለን ጨዋታውን
ሳይጀመር ሁለት ነጥብ ጥለን ነው ወደሜዳ
የምንገባው አሁን ፋሱል ከገባን በኋላ ግን
ከሜዳ ውጪ ይሁን ለማሸነፍ ብቸ ነው”
ብለውኛል፡፡ ይሄ ክለብ ውስጥ ያሸፈነውን
የአሸናፊነት ስሜት የሚጠቁም ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የፋሲል ከተማ ቡድን ፕሪምየር
ሊጉ ዘንድሮ በተቀላቀልኩት ሆነ ከነባር ቡድኖች
በበለጠ እንዴት በፍጥነት ፕሪምየር ሊጉን ሊላመድ
ቻለ ያለመቸገሩ ምክንያትስ ምንድነው?
ዘ-ማሪያም፡- በዋነኝነት ልጆቼ ጋር
ያለው አዲስ ታሪክ የማፃፍ ቁርጠኝነትና
ተነሳሽነት ነው፡፡ የደጋፊው የማሸነፍ ስሜት
ተመሳሳይ መሆኑን ረድቶኛል፡፡ ሱፐር ሊጉ
ላይ አብረው መቆየታቸው እያንዳንዱን
ጨዋታ ለማሸነፍ መጫወታቸውና በአንድነት
ለውጤት የመነሳታቸው ስሜት ይመስለኛል
ነገሩን ያቀለለው፡፡ በጣም የሚገርምህ ባለፈው
አመት ለዳሽን ቢራ የሚጫወቱ ልጆች
አሁን እኛ ጋር አሉ፡፡ ስለቡድኑ ወቅታዊ
ሁኔታ ከእነዚህ ተጨዋቾች ጋር ስናወራ
ቲሙ ውስጥ ባለው የማሸነፍ ስሜት በጣም
ነው የሚገረሙት፡፡ ተጨዋቾቹ ሲነግሩኝ
“ከዚህ በፊት ዳሽን ውስጥ ሆነን ስንጫወት
በተለይ ከታላላቅ ቡድኖች ጋር በሜዳችንም
ከሜዳችንም ውጪ ስንጫወት ቢያንስ
እንኳን አቻ ብንወጣ ብለን ነው የምንገባው፡
፡ አሁን ፋሲል ከገባን በኋላ ግን ከሜዳ
ውጪም ይሁን ስምና ውጤት ያለው ትልቅ
ክለብ ይሁን ወደሜዳ የምንገባው ለማሸነፍ
ብቻ ነው” ብለውኛል፡፡ ይሄ ክለቡ ውስጥ
የሰፈነውንነ የአሸናፊነት ስሜት የሚጠቁም
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከተማ አሁን በያዘው
ውጤት አድናቆት የሚሰጡት እንዳሉ ሁሉ ቡድኑ
ሁለት አይነት መልክ ያለው ነው፤ በሜዳውና
ከሜዳው ውጪ በማለት የሚተቹ አሉ፤ ትችቱን
ትቀበለዋለህ?
ዘ-ማሪያም፡-እደዚህ አይነቱ አስተያየት
ያሰጠው በሜዳችን ሁለቴ አቻ ስለወጣንና
ከሜዳችን ውጪ ያሸነፍንበት አጋጣሚ
ስላለ ይመስለኛል፡፡ እውነት ለመናገር
መሸነፍ በማይወደው ደጋፊ ፊት በሜዳችን
ስንጫወት ተጨዋቾቻችን ላይ ጫና ይኖራል፡
፡ ማሸነፍና ማሸነፍን ብቻ ለሚጠብቀው
ደጋፊ ተጨዋቾቻችን ማሸነፍ አለብን ብለው
ጓግተው መግባታቸው ጫናውን በማክበዱ
ነጥብ ያጣንበት ሁኔታ ስለ ተፈጠረ
ይመስለኛል እንደዚህ ዓይነት አስተያየቶች
እንዲሰጡ ያደረገው፡፡ ተጨዋቾቼ ከሜዳችን
ውጪ ሲንጫወት የተሻለ ነፃነት አግኝተው
ነው የሚጫወቱት ብዬ አስባለሁ፡፡ በሜዳችን
ነጥብ የጣልንባቸው ጨዋታዎች ከጉጉት
የተነሳ ብዙ ኳስ አምክነናል፡፡ ባለፈው
ከሐዋሳ ጋር ሲጫወቱ እኔ ለህክምና ወደ
ውጪ ሀገር ሄጄ ነበር፡፡ ግን የጨዋታውን
ቪዲዮ አይቼው ሙሉውን 90 ደቂቃ
ሲያጠቁ ቆይተው በሳቷቸው ኳሶች ነው
አቻ የወጡት፡፡ ይሄ አጋጣሚ ነው ስም
ያሰጠን እንጂ ሁለት መልክ ያለው ቡድን
ኖሮን አይደለም፡፡ እንደውም ከዚህ ጉዳይ
ጋር በተያያዘ በተለይ ከሜዳችን ውጪ
የማሸነፋችንን ምስጢር ልንገርህ…
ሀትሪክ፡- የሌሎች ክለቦች አሰልጣኞች
ምስጥሬን ይነጥቁኛል ብለህ ካልሰጋህ ደስ ይለኛል
ቀጥል…
ዘ-ማሪያም፡- ፋሲል ከተማ በሜዳውም
ከሜዳውም ውጪ ሲጫወት የማሸነፍ
ስሜትን ብቻ ነው ይዞ የሚገባው፡፡ በአገራችን
እግር ኳስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ አንድ
ያልተፃፈ ግን የተፃፈ የሚመስል ህግ አለ፡
፡ ክለቦች በሜዳቸው ሲጫወቱ ለማሸነፍ፤
ከሜዳቸው ውጪ ሲጫወቱ ግን አቻ
ወጥተው ነጥብ ተጋርተው መመለስን እንደ
ስኬት የሚቆጥሩበት ሁኔታ አለ፡፡ ይሄ ነገር
ግን ፋሲል ከተማ ጋር አይሰራም፡፡ ከሜዳችን
ውጪም በሜዳችንም ከማንም ጋር ይሁን
ለማሸነፍ ነው የምንጫወተው፡፡ ውጤታችንን
አጥብበን አንመኝም፡፡ በሰው ሜዳ ነጥብ
ነጥቆ አሸንፎ መመለስም ይቻላል የሚል
የጠነከረ ዕምነትና ባህል በክለባችን ውስጥ
አለ፡፡ የዛ ውጤት ይመስለኛል ከሰው ሜዳ
3 ነጥብ ይዘን እንድንመለስ የሚያደርገን፡
፡ ከማንም ጋር እንጫወት ቢያንስ ነጥብ
ተጋርተን እንመለስ ብዬ ልጆቼን መክሬ
አላውቅም፡፡ እነሱም በዚህ መንፈስ ወደ
ሜዳ ገብተው አያውቁም፡፡ ይሄን ስልህ ግን
የመጣን ውጤት በፀጋ አንቀበለውም ማለት
አይደለም፡፡
ሀትሪክ፡- ባሳካው የምትለው ቀጣይ እቅድህ
ምንድነው?
ዘ-ማሪያም፡- በቋሚነት የአገሪቱ ትልቁ
ሊግ ውስጥ ማለትም ፕሪምየር ሊጉ
ውስጥ መስራት ዋነኛ ምርጫዬ ነው፡
፡ ከዚህ ሌላ በጣም ቅርብ በሚባል ጊዜ
ደግሞ አገራዊ ውክልናን ተቀብዬ ብሄራዊ
ቡድኑን የማሰልጠን ትልቅ ህልም አለኝ፡፡
ይሄን የምለው ያለምክንያት አይደለም፡፡ ወደ
ስልጠናው አለም የገባሁት አስቤበት ከዚህ
ቦታ ተነስቼ እዚህ እደርሳለሁ ብዬ በመሆኑ
አሁን በቀጣይ እነዚህን ማሳካት የቅድሚያ
ዕቅዶቼ ስለሆኑ ነው፡፡ ከትንሽ ነገር ተነስቼ
ከፍ ወዳለ ነገር በመሄድ በሙያዬ ሃገሬን
ይበልጥ የማገልገል ረሃቡ ውስጤ አለ፤ ያንን
በአጭር ጊዜ ማስታገስ እፈልጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ዘማሪያም ከአሰልጣኝነት ይልቅ
በተጨዋችነት ከፍተኛ ደረጃ ይደርስ ነበር የሚል
መረጃ ሰምቼ ነበር፤ መረጃው እውነት ነው?
ለመሆኑ የት የት ተጫውተሃል?
ዘ-ማሪያም፡- ከመጨረሻው ጥይቄ
ልነሳልህ፡፡ በክለብ ደረጃ ታላላቅ ስም ላላቸው
ክለቦች በመጫወት አሳልፌያለሁ፡፡ ከእነዚህ
ውስጥ ለባንኮች፣ ለሙገር፣ ለኒያላ እና
ለወንጂ ስኳር ቡድኖች ተጫወቼ ጥሩ ጊዜን
አሳልፌያለሁ፡፡ ሌላው እንኳን ተመልካቹ
በቅርበት የሚያውቁኝ ሰዎች ቀርተው
እኔም ከአሰልጣኝነት ይልቅ በተጨዋችነት
ብዙ ርቀት እንደምጓዝ ነበር የማስበው፡፡
ነገር ግን የፈለገ ችሎታ ቢኖርም ትንሽዬ
እድል ካልታከለችበት የምትፈልገው ቦታ
ላይ አትደርስም፡፡ የተጨዋችነት ህይወቴ
በምፈልገው ደረጃ ብዙ ርቀት አልወደሰኝም
እንጂ አሁን ከምገኝበት የአሰልጣኝነት ደረጃ
በተሻለ ቦታ መገኘት ነበረብኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ለመሆኑ የብሄራዊ ቡድኑን ማሊያ
ለመልበስ ታድለሃል?
ዘ-ማሪያም፡- በብሄራዊ ቡድን ደረጃ
አሳዛኝ ገጠመኝን ነው ያለኝ፤ በአሰልጣኝ
ስዩም አባተ በሚሰለጥነው ወጣት ብሄራዊ
ቡድን እንድጫወት የመመረጥ እድሉን
ባገኝም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከልምምድ
በመቅረቴ የዲስፕሊን ችግር በሚል በመቀነሴ
አገር የመወከል እድልን አሳጥቶኛል፡፡ ይሁን
ቁጭቴን በአሰልጣኝነት ለማሳካት ግን ዛሬም
አልማለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የፕሪምየር ሊጉ አዲስ ድምቀት
የሆኑትን የፋሲል ከተማ ደጋፊዎች የድጋፍ
አሰጣጥን እዴት ነው የምትገልፀው የሚለውን
ጥያቄ የቆይታችን ማሳረጊያ ብናደርገውስ?
ዘ-ማሪያም፡- ከዚህ በፊት ለአንተም
እንዳልኩህ የፋሲል ከተማ ደጋፊዎች
በምድር ላይ ያሉ ቃላቶች በሙሉ ቢሰበሰቡ
በትክክል አይገልጿቸውም፤ ክለባቸውን
በፍቅር የሚወዱ ለክላባቸው ያላቸው ፍቅር
የእምነት ያህል ነው፡ የአፄዎቹ ለፕሪምየር
ሊጉ አዲስ ውበቶች አዲስ ከለሮች ልዩ
ድምቀቶች ናቸው፡፡ እውነት ለመናገር
ቡድኑ ነው እንጂ ወደኋላ የቀረው ደጋፊው
ፐሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው ቀድሞ ነው፡
፡ ቡድኑን ከራሱ በላይ አስበልጦ የሚወድ
እግር ኳስ እንደ ሻይ ሱስ ያህል የሚጠጣበት
ክለብን ነው ፕሪሚየር ሊጉ ያገኘው፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...