መነሻ ገጽ Uncategorized ​የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት አካዳሚበሳምንቱ መጨረሻ ይመረቃል ተባለ
Uncategorized

​የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት አካዳሚበሳምንቱ መጨረሻ ይመረቃል ተባለ

አጋራ
አጋራ


የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት አካዳሚ በሳምንቱ መጨረሻ ይመረቃል – በአቶ ይድነቃቸው ተሰማ የተሰየመው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት አካዳሚ በመጪው ማክሰኞ እንደሚመረቅ ክለቡ አስታወቀ፡፡

የክለቡ የሕዝብ ግንኑነት ኃላፊ አቶ ምንሊክ ግርማ እንደገለጹት ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የስፖርት አካዳሚ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡

በምረቃው ዕለት የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንደሚገኙ አቶ ምንሊክ አክለው ገልጸዋል፡፡

በመጪው ቅዳሜ መነሻቸውን መስቀል አደባባይ ያደረጉ 20 አውቶቡሶች ደጋፊዎችን በመያዝ ወደቢሾፍቱ ጉዞ እንደሚያደርጉም ታውቋል፡፡

አካዳሚው በቢሾፍቱ ከተማ በ24ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ከ100 በላይ ታዳጊ ስፖርተኞችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅም አለው፡፡

አካዳሚው ሁለት የእግር ኳስ ሜዳዎች፣ የምግብ አዳራሽ፣ የመሰብሰቢያ አዳረሽ፣ የመጫዎቻ ክፍሎች፣ መልበሻ ክፍል፣ ዘመናዊ የሕክምና ማዕከል እንዲሁም የጂምናዚየም ማዕከልን ያካከተተ እንደሆነ አቶ ሚኒሊክ አክለው ገልጸዋል፡፡ የግንባታው ወጪ በክለቡ ዳገፊዎችና አጋር ድርጅቶች እንደሸፈነ ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ክለብ የሆነው የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ክለብ በክለቦች ታሪክም የመጀመሪያውን የወጣቶች የስፖርት አካዳሚ በማስገንባትም ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ በ1928 ዓ.ም.እንደተመሰረተ ይታወቃል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...