መነሻ ገጽ Uncategorized የሊጉ መሪ ደደቢት ነጥብ ​ሲጋራ አሰልጣኙን ያሰናበተው ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል!
Uncategorized

የሊጉ መሪ ደደቢት ነጥብ ​ሲጋራ አሰልጣኙን ያሰናበተው ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል!

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች ቀጥለው ውለዋል።
ዛሬ በ9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያ አርባምንጭን ያስተናገደ ሲሆን፥ ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ የበላይነት ተጠናቋል።

ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ 2ለ1 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ፀጋዬ አበራ በ36ኛው ደቂቃ እንዲሁም ገብረሚካኤል ያዕቆብ በ41ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች አርባምንጭን አሸናፊ አድርገዋል።

መከላከያን በባዶ ከመውጣት የታደገችውን ጎል ሳሙኤል ታዬ በ78ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

ክልል ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ከቀኑ በ9 ሰዓት ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ በፋሲል ከነማ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ፋሲል ከነማን አሸናፊ ያደረገችውን ጎል ሄኖክ ገምቴሳ በ27ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

በተመሳሳይ ከቀኑ በ9 ሰዓት ወላይታ ዲቻ በሜዳው ሶዶ ስታዲየም ጅማ አባቡናንጠያስተናገደ ሲሆን፥ ጨዋታውም በወላይታ ዲቻ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል። የወላይታ ዲቻን የማሸነፊያ ጎልም በዛብህ መለዮ በ28ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

ይርጋለም ላይ የተደረገው የሲዳማ ቡና እና የኢትዮ ኤሌክትሪክን ጨዋታ ደግሞ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ በጨዋታው ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ፍጹም ገብረማርያም በ11ኛው ደቂቃ እንዲሁም አብይ በየነ በ85ኛው ደቂቃ ለሲዳማ ቡና የአቻነት ጎሎቹን ከመረብ አሳርፈዋል።

በሊጉ በጎል ልዩነት ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አዳማ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 2ለ1 በሆነ ውጤት ረቷል።

ለአዳማ ከተማ ሁለቱንም ጎሎች ቡልቻ ሹራ በ63ኛው እና በ88ኛው ደቂቃ ከመረብ ሲያሳርፍ፥ ለአዲስ አበባ ከተማ ደግሞ እንየው ካሳሁን በ75ኛው ደቂቃገአስቆጥሯል።

ከቀኑ በ10 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ላይ ድሬደዋ ከተማ ከደደቢት ተገናኝተው፥ ጨዋታው 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

እንዲሁም 11:30 ላይ ደግሞ አሰልጣኙን ያሰናበተው ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ከሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ጋር ጨዋታውን አድርጓል።

አሰልጣኙን ማሰናበቱን ይፋ ያደረገው ኢትዮጵያ ቡና በጊዜያዊነት ክለቡን እንዲያሰለጥኑ በተሾሙት አዲስ አሰልጣኝ እየተመራ ወደ ሜዳ ገብቶ ድል ተቀዳጅቷል።

ጨዋታውንም በአስቻለው ግርማና ጋቶች ፓኖም ሁለት ጎሎች፥ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በሊጉ ቀሪ አንድ ጨዋታ በነገው እለት የሚካሄድ ሲሆን፥ በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስወልዲያ ከነማን 11:30 ላይ በአዲስ አበባስታዲየም ያስተናግዳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...