መነሻ ገጽ Uncategorized ወልዲያ ከተማ በአዲሱ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማን ያስተናግዳል
Uncategorized

ወልዲያ ከተማ በአዲሱ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማን ያስተናግዳል

አጋራ
አጋራ

በ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገና ከነገ በስትያ ቀጥሎ ይደረጋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በሊጉ የደረጃ ሰንጠዥ መጨረሻ ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ነገ 9 ስአት ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል።

በተከታታይ ሰባት ጨዋታዎች የተሸነፈው አዲስ አበባ ከተማ እስካሁን 5 ነጥብ ብቻ ነው የሰበሰበው።

ሲዳማ ቡና በአንጻሩ በሊጉ ጥሩ ተፎካካሪ መሆን ቢችልም ባለፉት ሳምንታት ተከታታይ የጣለው ነጥብ ቀጣይ ጉዞውን አጠራጣሪ አድርጎታል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እንደተጠናቀቀ በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሊጉን መሪ አዳማ ከተማን ያስተናግዳል።

እሁድ ሊጉ ቀጥሎ 9 ሰዓት ላይ አራት ጨዋታዎች የሚስተናገዱ ሲሆን ደደቢት ከመከላከያ፣ ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ጅማ አባ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከፋሲል ከተማ ይጫወታሉ።

screenshot_2017-01-11-11-26-46

ወልድያ በአዲሱ ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም ከድሬዳዋ ከተማ ጋር እሁድ 11 ስአት ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።

የሊጉ 11ኛ ሳምንት የመዝጊያ ጨዋታ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወላይታ ዲቻን የሚገጥምበት ይሆናል።ሊጉን አዳማ ከተማ በ10 ጨዋታ 21 ነጥብ በመያዝ ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ20፤ደደቢት በ19 ነጥብ ይከተላሉ።

ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ጌታነህ ከበደ በ10፣አዳነ ግርማ በ5፣ ሳላዲን ሰይድ፣ገብረሚካኤል ያዕቆብ፣ ፍሬው ሰለሞንና ሌሎችም በ4 ጎሎች ይከተላሉ።

የደረጃ ሰንጠረዥ  እና የከፍተኛ ጎል አግቢዎች ይመልከቱ፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...