መነሻ ገጽ Uncategorized ወልዋሎ አ/ዩኒቨርሲቲ ተጨዋቾችን በመቀነስና በማምጣት ቅድመ ዝግጅታቸውን  አጠናክረው ቀጥለዋል
Uncategorized

ወልዋሎ አ/ዩኒቨርሲቲ ተጨዋቾችን በመቀነስና በማምጣት ቅድመ ዝግጅታቸውን  አጠናክረው ቀጥለዋል

አጋራ
አጋራ

ወልዋሎ  አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዙር የሊግ ጨዋታ ተጠናክረው ለመቅረብ  በአዲሱ አሰልጣኝ ፀጋየ ኪዳነማርያም እየተመሩ  በቀን 2 ጊዜ ቅድመ ዝግጅታቸውን እየሰሩ ነው፡፡
በሊጉ መጀመሪያ ሳምንታት ክስተት የነበሩት ወልዋሎ  አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች የሊጉ የመጀመሪያው ዙር አጋማሽ ጀምሮ ከሳምንት ሳምንት በውጤት ማጣት ቀውስ በመግባታቸው አሰልጣኝ እስከ መቀየር የደረሰ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የኘሪሚዬር ሊግ 15 ጨዋታዎች 16 ነጥቦችን በመሰብሰብ በ8 የግብ ዕዳ በደረጃ ሰንጠረዡ በ12ኛነት የተቀመጡት ወልዋሎ አ/ዩኒቨርሲቲዎች በሁለተኛው ዙር ተጠናክረው ለመቅረብ ተስፋ ያልተጣለባቸውን ተጨዋቾችን በመልቀቅ አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ እያመጡ ከመሆኑም ባሻገር በቀን 2 ጊዜ ልምምዳቸውን አጠናክረው እየሰሩ ነው፡፡
የቢጫዎቹ አዲሱ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም 3 አዲስ ተጨዋቾችን ፡ማናዬ ፋንቱን ከኢትዮጵያ ቡና፡አለምነህ ግርማ/ሶራ/ ከመቆለ ከተማ እና ታዲዬስ/ፔሌ/ን ከአርባ ምንጭ ከተማ ሲያስፈርሙ፡፡ 4 ነባር  ተጨዋቾችን ብሩክ አየለ ፡ቢኒያም አየለ ፡በለጠ ተስፋዬ ግብ ጠባቂውን እንዲሁም  እዬብ  ወ/ማርያምን ከስብስባቸው በተለያዩ ምክንያቶች ሲቀንሱ ሌሎች ተጨዋቾችንም የመቀነስ ዕቅድ እንዳላቸው አሰልጣኙ ፀጋዬ ኪ/ማርያም ገልፀዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...