መነሻ ገጽ Uncategorized ወላይታ ድቻ | ከወራጅ ቀጠና ፈቀቅ ያለበትን ድል ኢትዮ-ኤሌትሪክ ላይ አስመዘግቧል
Uncategorized

ወላይታ ድቻ | ከወራጅ ቀጠና ፈቀቅ ያለበትን ድል ኢትዮ-ኤሌትሪክ ላይ አስመዘግቧል

አጋራ
አጋራ

 በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በወላይታ ሶዶ ሁለ ገብ ስታዲየም  ወላይታ ዲቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1-0 አሸንፏል ።

ጎሏን በ36ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የተሻገረለትን ኳስ ወደ መሬት በማውረድ ያስቆጠረው ሰባት ቁጥሩ አናጋዉ ባደገ ነው።

በመጀመሪያዉ የጨዋታ አጋማሽ ወላይታ ዲቻዎች ኳስ በማደራጀት የተሻሉ ሲሆኑ ያገኟቸውን ዕድሎች ቢያስቆጥሩ ኖሮ የጎል ልዩነቱ ከዚህም ሊሰፋ ይችል ነበር።

በተለይ በመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች የኤሌክትሪክ በረኛ ስራ የበዛበት ሲሆን በ9ኛዉና 17ኛዉ ደቂቃ ላይ 23 ቁጥሩ ጸጋዬ ብርሃኑና 13 ቁጥሩ ዳግም በቀለ የሳቷቸዉ ኳሶች ደጋፊዎችን ያስቆጩ ነበሩ።

ኤሌክትሪክ በመከላከልና መልሶ በማጥቃት ወደ ጨዋታው ለመመለስ ቢሞክርም የተሻሉ የጎል ዕድሎችን ሳይፈጥር ቀርቷል።

የአስልጣኞች አስተያየት 

የወላይታ ዲቻ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ “ተጋጣሚያችንን ተጭነንና አጥቅተን በመጫወት ሙሉ ነጥብ ይዘን ለመውጣት ነበር የተዘጋጀነው ተሳክቶልናል” ብለዋል።

“ጎል ለማስቆጠር ካለን ጉጉት የተነሳ ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች እንዳንጠቀም ተጽዕኖ ፈጥሮብናል” ያሉት አሰልጣኙ ቀሪ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ስጋት ለመውጣት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ ብርሃኑ ባዩ “ወላይታ ዲቻ ረጃጅም ኳስ በመጫወት የሚያስቸግር ቡድን በመሆኑ ተከላክለን ነጥብ ለመያዝ ነበር አልተሳካልንም” ብለዋል

“በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ የተገኘውን አጋጣሚ ወደ ጎል መቀየር ያለመቻላችንና ሜዳው ለጨዋታ አመቺ ያለመሆኑ ዋጋ አስከፍሎናል” ብለዋል።

መልካም የሆነ የዳኝነት ሥነ-ሥርዓት  ማየታቸውን ገልጸው የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች የድጋፍ አሰጣጥ ለኳስ ዕድገት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል።

18199353_784360951727410_6569028884774601809_n

የደረጃ ሰንጠረዥ 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...