መነሻ ገጽ Uncategorized በፕሪሜየር ሊጉ ሲዳማ ቡናና ወላይታ ድቻ ድል ሲቀናቸው ኢትዮጵያ ቡናና ደደቢት ነጥብ ተጋርተዋል
Uncategorized

በፕሪሜየር ሊጉ ሲዳማ ቡናና ወላይታ ድቻ ድል ሲቀናቸው ኢትዮጵያ ቡናና ደደቢት ነጥብ ተጋርተዋል

አጋራ
አጋራ

 

በ26ኛ ሳምነት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሲካሔድ የመጀመሪያው ጨዋታ የነበረው በ8፡30 በአዲስ አበባ ስታድየም የተካሄደው

ethiopian-coffeejima

በኢትዮጵያ ቡና እና በጅማ አባ ቡና    በኩል የተደረገውጨዋታ ነበር ከጨዋታው  መጀመር አስቀድሞ በቅርቡ ሂወቱ ላለፈው  የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ  ቢኒያም የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጎለታል ።

FB_IMG_1493587056019

ጨዋታው ከተጀመረ ቡሃላ የታየው እንቅስቃሴ ብዙም ማራኪ አልነበረም  በጨዋታው ላይ ጅማ አባ ቡናወች የተሻለ የኳስ ቁጥጥር  ቢያደርጉም ወደጎል  በሚደረጉ  ሙከራወች የታጀበ አልነበረም። በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱ  ቡድኖች መጀመሪያ ከነበረው የተሻለ እንቅስቃሴ እና የጎል ሙከራዎችን ማሳየት ችለው ነበር  ሆኖም ሁለቱም ቡድኖች ግብ  ሳያስቆጥሩ ቀርተው  ነጥብ ተጋርተው ሊወጡ ችለዋል።

sidama-bunna-sc

addis-ababa-city-football-club-l-1

በሻምፒዮንነት ፉክክር ውስጥ የሚገኘው ሲዳማ ቡና በሊጉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘውን አዲስ አበባ  ከተማን አስተናግዶ በሊጉ ወደ 2ኛ ደረጃ ከፍ ማለት የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል። በጨዋታው መጀመሪያ አዲስ አበባ  ከተማዎች ጨዋታውን መቆጣጠር ችለው ነበር ጨዋታው በተጀመረ በ18ኛው ደቂቃ በአጥቂው ሃይሌ እሸቱ አማካኝነት መምራ ችለው ነበር   ሆኖም መሪነታቸውን አስቀጥለው መቆየት የቻሉት እስከ 37ኛው ደቂቃ ብቻ ነበር  በ37ኛው ደቂቃ በናይጄሪያዊው ላኪ ሳኒ አማካኝነት ባስቆጠሩት ግብ አቻ ሆነው ለእረፍት ወደ   መልበሻ   ቤት ገብተዋል።  ከእረፍት መልስ ሲዳማ ቡናዎች  የተሻለ እንቅስቃሴ አሳይተዋል በ 48ኛው ደቂቃም ላኪ ሳኒ ለራሱም ለቡድኑም 2ኛውን ግብ በማስቆጠር ሲዳማ ቡናን መሪ ማድረግ ችሏል።  በ61ኛው ደቂቃላይ አዲስ ግደይ ቡድኑ ሲዳማ ቡና መሪነቱን ያሰፋበትን 3ኛ ጎል በራሱ የግል ጥረት አስመዝግቦ ቡድኑንአሽናፊ አድርጎታል።

adama-city-football-club-logo-12.png combank-logo

በሌላ ጨዋታ 9ሰአት ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ 1 እኩል በሆነ ውጤት ሲጠናቀቅ በጨዋታው ቅድሚያ  ግብ  ማስቆጠር   የቻሉት  ንግድ ባንኮች በ56ኛው ደቂቃ ላይ በጂብሪል አህመድ አማካኝነት  ነበር ሆኖም መደበኛው 90ደቂቃ አልቆ   በተጨመሪ 2ደቂቃ ታፈሰ ተስፋዬ  ባስቆጠረው አንድ ግብ  ሁለቱ  ክለቦች ነጥብ ተጋርተው መውጣት ችለዋል።  በጨዋታው ላይ ደጋፊወች  ” ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ከሙስና የፀዳ ትውልድ እናፍራ ”   የሚል ባነር  በስታዲየም  ውስጥ  አሳይተዋል።

DEDEBIT FC 74ac6f4d-d2c1-4a26-aff7-10dd4ee7f2adበ10:30 በአዲስ አበባ ስታድየም መከላከያ እና ደደቢት ባደረጉት ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።   በጨዋታው መከላከያ የተሻለ የኳስ እንቅስቃሴ ማሳየት ችሎ ነበር። ሆኖም የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ 0ለ0 በሆነ  አቻ  ውጤት  ተጠናቋል።  በጨዋታው  በመከላከያ በኩል  በ87 ደቂቃ አወል አብደላ  የቢጫ ካርድ ሰለባ ሲሆን በደደቢት  በኩል ብርሃኑ  ቦጋለ በ45ኛው ደቂቃ  ሰለሞን ሃብቴ በ63ኛው እንዲሁም ሺመክት ጉግሳ በ76ኛው ደቂቃ የቢጫ ካርድ ሲመለከቱ  ዳዊት ፍቃዱ በ82ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ከጨዋታው መጠናቀቅ ቡሃላ ጨዋታውን ማሽንፍ ትችሉ ነበር ነጥብ ተጋርታችሁ መውጣታችሁ ተገቢ አይደለም  በሚል ምክንያት የተናደዱ አንዳንድ የሲዳማ ቡና ደጋፊወች ባነሱት ፀብ  ምክንያት  በተወረወሩ ድንጋዮች  የመከላከያ ተጨዋቾች የሚጠቀሙበት ሰርቪስ መስታወት ተሰብሯል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...