መነሻ ገጽ Africa ኳታር 2022| የጋና አለም ዋንጫ ታሪክ ዳሰሳ
Africaአፍሪካአፍሪካ ዋንጫየአለም ዋንጫ ማጣሪያጋና

ኳታር 2022| የጋና አለም ዋንጫ ታሪክ ዳሰሳ

አጋራ
አጋራ

 

በኳታር አሰተናጋጅነት ለሚከናወነው 34ኛው የአለም ዋንጫ ለመካፈል በምድብ 7 ኢትዮጵያ ከጋና ደቡብ አፍሪካ እና ዙምባዌ ጋር መደልደሏ ዛሬ ካይሮ ላይ የነበረው እጣ ማውጣት ስነስርአት አሳውቋል። የሀትሪኩ ሚሊዮን ኃይሌ በምድቡ ውስጥ ከተካተቱት ሀገራት በቻርለስ አክኖር የምትሰለጥነው ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና የአለም ዋንጫ ተሰትፎ ምን ይመስላል ሚለውን ነገር በቀዳሚነት አንስቶ አዘጋጅቶልናል።

አለማቀፍ ተሳትፎ አጀማመር ታሪክ

ጋና በአለማቀፍ ውድድሮች መሳተፍ የጀመረችው በ1950። ጋናዎች ብላክ ስታርስ (black stars) የሚል ቅጥያ ስምም አላቸው። ጋና በአለማቀፍ ግንኙነት ለመጀመሪያ ግዜ የገጠመችው ብሄራዊ ቡድን ብርትሽ ቶጎላንድን ነበር። በዛ ጨዋታም ጋና 1-0 አሸነፋ እንደነበር አይዘነጋም። በታሪኳ ኔዘርላንድን 12-0 ያሸነፈችበት ትልቁ ድሏ ሲሆን። በቡልጋሪያ 10-0 የተሸነፈችበት ጨዋታ ደግሞ አስከፊው የታሪክ ወጤቷ ነበር።

የአለም ዋንጫ እና የጋና ትውውቅ

ጋና ከአለም ዋንጫ ተሳትፎ ጋር ሀ ብላ መተዋወቅ የጀመረችው ጀርመን ባሰናዳችው 26.29 ቢሊዮን ተመልካቾች የተመለከቱት።ጣልያን ከፍ አድርጋ ያነሳችው የ2006 አለም ዋንጫ ላይ ነበር። በ2006,2010,2014 በተከታታይ ሶስት አመት መሳተፍ የቻለች ጠንካራ ሀገር ነች። ጣልያንን ተከትላ በስድስት ነጥብ በሁለተኝነት ምድቡን ብታጠናቅቅም በብራዚል 3-0 ተሸንፋ ከውድድሩ ውጭ ሆናለች።

የጋና ጥሩ ውጤት

በአህጉራችን አፍሪካ ለመጀመሪያ ግዜ የተሰናዳው የ2010 አለም ወንጫ ለአፍሪካውያን በተለይ ደግሞ ለጋናውያን አስደሳች የሚባል ውጤት ነበር። ምንም እንኳን ጋና በኡራጋይ በፍፁም ቅጣት ምት ከውድድሩ ብትሰናበትም እሩብ ፍፃሜ መቀላቀል የቻለች ሶስተኛ አፍሪካዊት ሀገር አንዷ እንደነበረችም አይዘነጋም። ይህ በጋና እግር ኳስ በደማቅ ታሪክ የተፃፈ ጥሩ ውጤት ሆኖ ያለፈ ነው።

የጋና አስከፊው ውጤት

ጋና አሰከፊው የአለም ጨዋንጫ ጉዞዋ በ2014 አሜሪካ ጀርመን እና ፖርቹጋል በነበሩበት ምድብ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ በጊዜ ከምድቧ የተሰናበተችበት ውጤት ነው።

ጋና በ2022 አለም ዋንጫ

ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባዌ ሚገኙበት ምድብ 7 የምትገኘው ጋና ኳታር በምታስተናግደው አለም ዋንጫ በቀላሉ የማለፍ እድል እንዳለት ግምቶች ተሰጥቷታል።

የሀገሪቱ ተጠባቂ ተጫዋች አሳሟጂያን

አሳሟጂያን በ109 ጨዋታዎች ተሰልፎ በመጫወት 51 ግቦችን ኳስና መረብ ያገናኘ ብቸኛ የጋና ተጫዋች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጠበቂ ያደርገዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
አፍሪካ ዋንጫአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ ከሜዳቸው ውጪ ድል ቀንቷቸዋል

በገለልተኛ ሜዳ ሞሮኮ ላይ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን በአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የገጠመው...

Afconአፍሪካ ዋንጫዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ኢትዮጵያ ነገ ተጋጣሚዋን ታውቃለች

በሦስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አዘጋጅነት ለሚደረገው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በአህጉሪቱ የሚገኙ...