በሦስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አዘጋጅነት ለሚደረገው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በአህጉሪቱ የሚገኙ ዝቅተኛ ሀገራት የሚገናኙበት የቅድመ ማጣሪያ መርሀግብር ነገ ይፋ ይሆናል።
ካፍ ከቀጣዩ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በየአራት አመቱ የአፍሪካ ዋንጫ እንዲደረግ በቅርቡ ውሳኔን ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን አሁን እየተደረገ ካለሁ የሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ ቀጥሎ በኬኒያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አስተናጋጅነት ከሁለት አመት በኋላ የሚደረገውም የመጨረሻው ይሆናል። ሦስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በጣምራ በሚያዘጋጁት በዚህ ውድድር ላይ በምድብ ማጣሪያ አርባ ሁለት ሀገራት የሚካፈሉ ሲሆን የምድብ ድልድሉ ውስጥ ለመግባትም በፊፋ ወቅታዊ የእግር ኳስ ደረጃ ዝቅተኛ ተብለው የሚጠሩ አስራ ሁለት የአህጉሪቱ ሀገራትን የሚያካፍለው የቅድመ ማጣሪያ ድልድል የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአት ነገ ሞሮኮ ላይ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይከናወናል።
በማጣሪያው ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሴቶ ፣ ብሩንዲ ፣ ኢስዋቲኒ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሞሪታንያ ፣ ቻድ ፣ ሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ ፣ ጅቡቲ ፣ ሱማሊያ ፣ ሲሼልስ እና ወደ ወድድር እንደምትመለስ የምትጠበቀው ኤርትራ ተፈላሚዎቹ ሀገራት ናቸው። በሁለት ቋት የተከፈለው እና ዋልያዎቹን በቋት አንድ ያስቀመጠ ሲሆን ምናልባትም ከሶማሊያ ፣ ሳኦቶሜ ፣ ሶማሊያ ፣ ሲሼልስ ፣ ቻድ እና ጅቡቲ አንዳቸው ሊደርሳት እንደሚችል ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ