ፋሲል ከነማ በኢትዮጵያ ቡና የተሸነፍኩት አግባብነት የለውም በሚል ያቀረበው ቅሬታ ውድቅ ሆኗል።
ፋሲል ከነማ ከሁለት ቀናት በፊት ቅዳሜ 10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሀግብሩን በኢትዮጵያ ቡና የሊጉን የመጀመሪያ ሽንፈት አሰልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌን በሸኙ ማግስት ማስተናገዳቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ቡናን እየመሩ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ድል ያደረጉት አዲሱ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ በ2016 ኢትዮ ኤሌክትሪክን እየመሩ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ባሳደጉበት አመት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የማጠቃለያ የዋንጫ ጨዋታ ወቅቱ ቡድናቸው በአርባምንጭ ከተማ ተሸንፎ ዋንጫውን ባጣበት ሲያጣ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ በወቅቱ የስድስት ጨዋታዎች ቅጣትን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን መጣሉ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ ፋሲል ከነማ በከፍተኛ ሊግ ወቅት አሰልጣኙ የስድስት ጨዋታዎች ቅጣት ተጥሎባቸው ቅጣታቸውን ሳይጨርሱ ክለቡን በፕሪምየር ሊጉ መምራት አልነበረባቸውም ስለዚህ ነጥቡ በፎርፌ ሊሰጠኝ ይገባል ሲል ክስ አሰምቷል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቡና ከጨዋታው ቀደም ባሉ ቀናት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የአዲሱን አሰልጣኝ ውል ሲያፀድቅ አያይዞ አሰልጣኙ ከአራት ወራት በላይ ያለ ስራ ማሳለፋቸው እንደ ቅጣት ተቆጥሮ ነፃ መባላቸውን በደብዳቤ በማሳወቁ የፋሲል ከነማ አቤቱታም ተቀባይነት ማግኘት ሳይችል ቀርቷል።


