መነሻ ገጽ Uncategorized ካሜሮን ለ5ኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አነሳች
Uncategorized

ካሜሮን ለ5ኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አነሳች

አጋራ
አጋራ

ካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫን ለአምስተኛ ጊዜ አንስታለች። እሁድ ፍጻሜውን ባገኘው የጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ ግብፅ እና ካሜሩን ለዋንጫ ቀርበው በካሜሮን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ጨዋታው ተጠናቋል።

cameroon_3.jpg

በጨዋታው የግብፅ ብሄራዊ ቡድን (ፈረኦኖች)ቀደመው በ22ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥረው መምራት ችለው ነበር።

በጉዳት ምክንያት ሁለት ጨዋታ ያለፈው የግብፅ  ብሄራዊ ቡድን አማካይ መሃመድ ኤል-ኒኒ በጥሩ መልኩ ከመሃመድ ሳላህ የተቀበለውን ኳስ አስቆጥሮ ግብፅን በመጀመሪያው አጋማሽ መሪ ማድረግ ችሏል።

ሆኖም ግን በሁለተኛው አጋማሽ የካሜሮን ብሄራዊ ቡድን (ማይበገሩት አንበሶች) ሙሉ ለሙሉ ተጭነው  በመጫወት በጫወታው ላይ ብልጫ ወስደዋል።

ካሜሮንን ከግብፅ ጋር አቻ ያደረገችው ጎልም በ58ኛው ደቂቃ ተከላካዩ ኒኮላስ ንኮሉ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሯል።

የግብፅ ብሄራዊ ቡድን (ፈረኦኖች) ጨዋታው በአቻ ውጤት እንዲጠናቀቅ በመከላከል ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።

መደበኛው የጨዋታ ሰዓት ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ሲቀሩ ተቀይሮ ወደ የገባው ቪንሶን አቡበከር በ88ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል ካሜሮንን ሻምፒዮን ማድረግ ችሏል።

በዚህም መሰረት የማይበገሩት አንበሶች ካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫን ሰባት ጊዜ ያነሱትን የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ፈርኦኖችን በመርታት የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነዋል።

cameroon_4.jpg

በትናንት ምሽቱ የፍጻሜ ጨዋተታም ካሜሮን ከ15 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማሸነፍ ችላለች፡፡

ካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫን ስታነሳ የአሁኑ አምስተኛዋ ነው።

በ31ኛው የቶታል የአፍሪካ ዋንጫ ሶስት ጎል ብቻ የገባበት የ44 ዓመቱ የግብ ጠባቂ ኤሳም ኤል-ሃዳሪ የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ተብሎ የተመጠረ ሲሆን፥ የካሜሮኑ አጥቂ ክሪስቲያን ባሶጎግ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡

በተያያዘ ቅዳሜ ምሽት የተደረገው የደረጃ ጨዋታም ቡርኪና ፋሶ ጋናን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

እንዲሁም በውድድሩ ጋና 4ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...