ከ20 በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ቤሕራዊ ቡድን 10:00 ላይ ከቡሩንዲ አቻው ጋር ይገጥማል እኛም ጨዋታውን የተመለከተ ጉዳዮችን አንሰተናል ።
ዛሬ ከቀኑ 10:00 ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የቡሩንድ አቻውን ቡሩንዲ ቡጁምቡራ ላይ ኢንዋሪ ስታድየም የአለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያውን ያደርጋል። ዛሬ አራት ስአት ላይ ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ የተደረገ ሲሆን ቤህራዊ ቡድናችን ሙሉ ቢጫ መለያ አድርጎ እንደሚገባ ሲነገር የቡሩንዲ አቻው በአንፃሩ ነጭ ማሊያ አረንጓዴ ቁምጣ እና ቀይ ካሶቶኒ በመልበስ ወደ ሜዳ ይገባሉ ። ጨዋታውን የሚመሩት ኡጋንዳዊያን ዳኞች መሆናቸው ሲነገር ትላንት ምሽት አራት ስአት ላይ ቡጁምቡራ መድረሳቸውም ታውቋል። ብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን በሚጫወቱበት ኢንዋሪ ስታዲዮም የሰሩ ሲሆን። ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤነኝነት ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን ሀትሪክ ስፖርት ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል። ሀትሪክ ስፖርትም ለብሔራዊ ቡድናችን መልካም ውጤት በመመኘት ጨዋታውን በቀጥታ የውጤት መግለጫ የመታስተላልፍላቹህ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ