መነሻ ገጽ Uncategorized ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግምታዊ አሰላለፍና ቅድመ ዳሰሳ
Uncategorized

ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግምታዊ አሰላለፍና ቅድመ ዳሰሳ

አጋራ
አጋራ

ግምታዊ አሰላለፍ

ከሰሞኑ ከተመለከትናቸው ነገሮች መነሻ ቡድኖቹ በሚከተሉት አሰላለፎች ጨዋታውን እንደሚጀምሩ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና፡– ( 4-3 -3)

ቡናማዎቹ ባለፈው ሳምንት ድሬዳዋ ከተማን ሲገጥሙ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ሁለት ያለቁ የጎል ሙከራዎችን በመመለስ ቡድኑን ካልተጠበቀ ሽንፈት ያዳነው ግብ ጠባቂያቸው ሀሪስተን ኮአሲ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል፡፡ በጉዳት በማይሰለፈው አብዱልከሪም መሀመድ ምትክ ሳላምላክ ተገኝ ሊጫወት ይችላል፡፡ ከፊት አሰልጣኝ ቩቺቼቪች ምናልባትም በሳዲቅ ሴቾ ፈንታ ዊልያም ያቡንን ይጠቀሙ ይሆናል፡፡


ግብ ጠባቂ፡ – ሀሪስተን ኮአሲ

ተከላካዮች፡ – ሳላምላክ ተገኝ፣ ኢኮ ፊቨር፣ ኤፍሬም ወንድወሰን እና አህመድ ረሺድ

አማካዮች፡- ጋቶች ፓኖም፣ አማኑኤል ዮሀንስ እና ኤልያስ ማሞ

አጥቂ፡- እያሱ ታምሩ፣ ዊልያም ያቡን እና ሳሙኤል ሳኑሚ

ቅዱስ ጊዮርጊስ፡ – ( 4 -3-3)

ምንተስኖት አዳነ የመሀል ተከላካይ ስፍራን የራሱ ያደረገ መስሏል፡፡ ከጉዳቱ ድኖ መጫወት የጀመረው ሰልሀዲን ባርጊቾ በመሀል ተከላካይ ስፍራ ምንተስኖትን ሊጣመር ይችላል፡፡

ሳሙኤል ሳኑሚ በክንፍ የሚፈጥረውን ስጋት ለመከላከል አሰልጣኝ ማርት ኖይ አስቻለው ታመነን በቀኝ ተከላካይ ስፍራሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ 

አማካይ ክፍል ላይ ከጉዳት የተመለሰው ምንያህል ተሾመ ሊሰለፍ ይችላል፡፡ ምንያህል ለጨዋታ ብቁመሆኑ አጠራጣሪ ከሆነ ግን አሰልጣኙ ሙጌርዋን መጠቀምን ይመርጡ ይሆናል፡፡ 

በአጥቂ ስፍራ በኃይሉ አሰፋ በጉዳት ምክንያት መግባቱ አጠራጣሪ ስለሆነ አዳነ ግርማን በተሰላፊነት ሊጀምር ይችላል፡፡


ግብ ጠባቂ፡ – ሮበርት ኦዳንካራ

ተከላካዮች፡ – አስቻለው ታመነ፣ ምንተስኖት አዳነ፣ ሰልሀዲን

ባርጊቾ እና አበባው ቡታቆ

አማካዮች፡- ናትናኤል ዘለቀ፣ ምንያህል ተሾመ/ያስር ሙጌርዋ

እና አብዱልከሪም

አጥቂዎች፡ – አቡበከር ሳኒ፣ አዳነ ግርማ እና ሰልሀዲን ሰኢድ

ጉዳት እና ቅጣት

በኢትዮጵያ ቡና በኩል የቀኝ ተከላካዩ አብዱልከሪም መሀመድ ( ቁርጭምጭሚት ) እና አማካዩ መስኡድ መሀመድ ( ጉልበት ) በጉዳት ምክንያት በዚህ ጨዋታ አይኖሩም፡፡

 በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል የቀኝ መስመር አጥቂው በኃይሉ አሰፋ በጉዳት ምክንያት በዚህ ጨዋታ ላይ አይገኝም፡፡

ነጥብ እና ደረጃ

ከሰባት ሳምንታት የሊጉ ጉዞ በኋላ ኢትዮጵያ ቡናዎች በሰባት ነጥቦች 12 ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በ14 ነጥቦች አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የቅርብ ጊዜ ውጤቶች

ባለፈው ዓመት ሁለቱ ቡድኖች ባደረጓቸው የሊግ ጨዋታዎች ሁለቱንም በአቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡ በሁለቱም ጨዋታዎች ምንም ጎል አልታየም፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...