በመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ደካማ ውጤት እያስመዘገበ እሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በሁለተኛው ዙር ተጠናክሮ እንደሚያቀርቡ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ተናግረዋል
” ክለባችን/አዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ /በሁለተኛ ዙር የፕሪሜር ሊግ ጉዞው ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀርብ ዘንድ በሚያስፈልጉን ስፍራዎች..ከጋና፣ከማሊ፣ከኮንጎ..ተጨዋቾች ማስፈረም ችለናል…/በሀገር ውስጥ ገበያ ስለተቀደምን/እስካሁን በነበረን ጉዞም ተጨዋቾቼ የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ መቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የነዚህ 4/አራት/አዲስ ተጨዋቾች ወደ ክለባችን መምጣት ተጨማሪ ኃይል እንደሚፈጥርላቸው ተስፋ እያደረኩ…እስካሁን ድጋፋችሁ ላልተለዬን የስፖርት አፍቃሪዎችም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።”
በሚል ቃል የክለባቸውን መጠናከር ገልፀዋል።

አስተያየት ይስጡ