መነሻ ገጽ Uncategorized አበረታች መድሀኒት የሚጠቀሙአትሌቶች የእድሜ ልክ እገዳይጣልባቸዋል ተባለ
Uncategorized

አበረታች መድሀኒት የሚጠቀሙአትሌቶች የእድሜ ልክ እገዳይጣልባቸዋል ተባለ

አጋራ
አጋራ

 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንአበረታች መድሀኒት ሲጠቀሙ ለተገኙ አትሌቶች ምንም አይነት ይቅርታ አያደርግም አሉ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሻለቃ ሀይሌ  ገብረ ስላሴ።

በወቅታዊው የፀረ – ዶፒንግ እንቅስቃሴ ዙሪያ ፌዴሬሽኑ ትናንት ለውጭ ሃገርና ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህ ወቅት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሻለቃሀይሌ ገብረ ስላሴ፥ አበረታች መድሃኒትተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች የእድሜ ልክ እገዳ እንደሚጣልባቸው ተናግረዋል።ፌዴሬሽኑ ለእውነተኛ እና ንፁህ አትሌቶች መብት መከበር ግን በማንኛውም ሁኔታ እስከ፡መጨረሻ ድረስ ይሟገታልም ነው ያሉት።

ከዚህ በኋላ ከአበረታች መድሃኒቶች እና ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ከተጠረጠሩ አትሌቶች፣ ማናጀሮች እና አሰልጣኞች ጋር ፌዴሬሽኑ አብሮ የማይሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ከብሄራዊ የፀረ- አበረታች መድሃኒት ፅህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት እንደ አውሮፓውአቆጣጠር በ2017 200 ናሙናዎችን በመውሰድ ምርመራ ለማስራት ማቀዱንም ነው የገለጹት።

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን እና ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር የእገዳ ቅጣት በተጨማሪ የኢፌዴሪ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 526ን መሰረት በማድረግ ከአበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ጋር ተያይዞ ወንጀል የሰራ ማንኛውም አካል በኢትዮጵያ ህግም ተጠያቂ ይሆናል ብለዋል ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...