መነሻ ገጽ Uncategorized ነገ (ማክሰኞ ሰኔ 20/2009) ዓ.ም ለንባብ ከምትበቃው ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ይጠብቋታ
Uncategorized

ነገ (ማክሰኞ ሰኔ 20/2009) ዓ.ም ለንባብ ከምትበቃው ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ይጠብቋታ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዳሜ ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮን አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ ወራጅ መሆናቸውን አስቀድመው አውቀዋል፡፡ ቀሪዎቹ ሁለት ወራጅ ቡድኖች በፍፃሜው ዕለት ተለይተው ታውቀዋል፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንድ ድራማዎች እንደነበሩ ሲነገር ነበር፡፡ ለምሳሌ ወላይታ ዲቻ ደደቢትን አስተናግዶ 4-2 በረታበት ጨዋታ ዲቻዎች ጌታነህ ከበደ ለ16 ዓመታት የቆየውን የዮርዳኖስ አባይን የ24 ጎሎች ሪከርድ እንዲሰብር ሁለት ጎሎች ሊለቁለት፤ ደደቢት ደግሞ ተሸንፎላቸው ከመውረድ ሊያድናቸው ተስማምተው ገብተው ያንን ተፈፃሚ አድርገዋል የሚሉ ወሬዎች በስፋት በመናፈስ ላይ ይገኛሉ፤ ለመሆኑ በዕለቱ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ በ25 ጎሎች ሪከርዱን በእጁ ያስገባው ጌታነህ ከበደ በዚህ ዙሪያ ምን ይላል? ከጨዋታው ማግስት ለመጀመሪያ ጊዜ ነገ (ማክሰኞ ሰኔ 20/2009) ዓ.ም ለንባብ ከምትበቃው ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ጋር ቃለ-ምልልስ አድርጓል፤ ያንብቡት፡፡
– በፕሪሚየር ሊጉ የፍፃሜው ቀን ኢት.ንግድ ባንክ መውረዱ ብዙዎቹን አሳዝኗል፡፡ ካዘኑት መካከል ደግሞ የቀድሞው የክለቡ ተጨዋች እና የኮሚቴ አባል የነበረው ሸዋረጋ ደስታ አንዱ ነው፡፡ በሀዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ ከሀትሪክ ጋር ቆይታ ያደረገው ሸዋረጋ “የክበብ ቀይ ወጥ እየበላን፤ እንደ አትክልት ሜዳ ላይ በጎማ ውሃ እየታጠብን ያወጣነውን ክለብ ቴላቴሊና ሰኮንዶ እየበሉ አወረዱት” ሲል ለችግሩ ተጠያቂዎች ናቸው የሚላቸውን አመራሮች ይተቻል፡፡ እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው? ባንክ እንዴት እንደዚህ ለውድቀት ሊዳረግ ቻለ? የችግሩ መንስኤ ምንድነው? መፍትሄውስ? ክለቡስ ሊፈርስ ይችል ይሆን? በእነዚህና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ዙሪያ የቀድሞው የክለቡ ተጨዋች ሸዋረጋ ደስታ የጋዜጣዋ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ በድፍረት ላቀረበለት ጥያቄዎች እሱም በድፍረት ምላሹን ሰጥቷል፤ አስገራሚ ቃለ-ምልልስ ነው፤ እንዳያመልጦት፡፡
– በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ለኮከብ ተጨዋችነት ግምት ከተሰጣቸው ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የቅ/ጊዮርጊሱ ተከላካይ አስቻለው ታመነም ከእኛ ጋር ቆይታ ያደረገ ሌላኛው ተጨዋች ነው፡፡ “ሻምፒዮናው ቅ/ጊዮርጊስ ታሪክ ሰሪ፤ ለማልያቸውም ሟች የሆኑ ተጨዋቾችን ያሰባሰበ በመሆኑ ክለቡን ይበልጥ እንድወደው አድርጎኛል” ይላል፡፡ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያም ይናገራል፤ ይወዱታል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በነገው ዕትሟ ከባህር ማዶም በርካታ ያልተሰሙ ዜናዎችን ይዛለች፡፡ ነገ ማክሰኞ ሰኔ 20/2009 ዓ.ም በማለዳው ከእጅዎ የምትገባው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገጿ ይሄንን ይመስላል፡፡

 በተጨማሪም በድረ-ገፃችን www.hatricksport.com በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነው ያለፉ ሙሉ ዕትሞቻችንን ጨምሮ ትኩስና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ስፖርታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ፤ መልካም ጊዜ!

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...